ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ለሶሻል ሚዲያ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች [Video]

ሌፍተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ‹‹የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ፤ የሀገሪቱ እና የኢሕአዴግን ያለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ጉዞ በወፍ በረር ከቃኙ በኋላ፤ አሁን ሀገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ ቀውስና አደጋዎች የመፍትሔ ሀሳብ ይሆናል ያሉትን ማቅረባቸውና ፖለቲካዊ መፍትሔዎችን ለማስፈፀምም ‹‹በሀገራችን ካሉት የተለያዩ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች ተስማምተው የሚቋቋሙት ይህንን ሂደት የሚመራ መዋቅር መፈጠር አለበት›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ተከትሎም አንባቢዎች በሆርን አፌይርስ፣ በሶሻል ሚዲያ፣ ወዘተ የተለያዩ ትችቶችንና ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል፡፡

ጻድቃን ባለፈው እሮብ በተለይ ለሆርን አፌይርስ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ለትችቶቹና ጥያቄዎቹ ምላሽና ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡

[ቪዲዮውን ይመልከቱ (link)]

ዋና ዋና ነጥቦች

* የፖለቲካ መፍትሔ ሀሳቡን ያቀረቡት ህወሓትን ለማዳን ወይም ለህወሓት ግዜ ለመግዛት ነው የሚል ትችት ይቀርባል፡፡ ከአሜሪካኖች ተማክረው ያቀረቡት ነውም ይባላል፡፡ (ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ)

* ጽሑፉ ከታተመ በኋላ ምን ዓይነት ግብረ-መልሶችን አገኙ? – (ከ3:18 ደቂቃ ጀምሮ)

* ጄ/ል ጻድቃን ራሳቸውን ከኢሕአዴግ ድርጊቶች ነጻ አድርገው እያቀረቡ ነው ወይ? ለምሳሌ ኦነግ ከሽግግር መንግስት ሲወጣ አብረው ነበሩ፡፡ (ከ10፡48 ደቂቃ ጀምሮ)

* የመፍትሔ ሀሳቡን ተግባራዊ አፈጻጸም እንዴት ይሆናል? ከህገ-መንግስቱ ጋር ይሄዳል? ፓርላማው ይፈርሳል? (ከ16፡38 ደቂቃ ጀምሮ)

* ኢሕአዴግ የመፍትሔ ሀሳቡን ለመቀበል ባህርይው ይፈቅድለታል ወይ? (ከ28፡33 ደቂቃ ጀምሮ)

* ከመፍትሔ ሀሳቡ በተያያዘ ተጨማሪ አስተያየት::  (ከ33፡48 ደቂቃ ጀምሮ)

* ጄ/ል ጻድቃን ራሳቸው ከስርዓቱ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አይደሉም ወይ? (ከ38፡16 ደቂቃ ጀምሮ)

——

Watch the Video 

*************

Daniel Berhane

more recommended stories