(በስንታየሁ ግርማ)

የ2015 የፈረንጆቹ ዓመት ለአርሴናል ደጋፊዎች እጅግ አስደሳች ነበር ፡፡ እኔ ለእግር ኳስ የተለየ ፍቅር አለኝ ፡፡ ዘመኑ የግሎባላይዜሽን በመሆኑ በአለም ላይ የሚደረጉ ድርጊቶችን በሙሉ እንድከታተል እና እራሴን አንዱ የእግር ኳስ አካል እንዳደርግ ረድቶኛል፡፡እኔ ቀንደኛ የአርሰናል ደጋፊ ነኝ አርሰናልን ከምደግፍበት ምክንያቶች መካከል አንዱ ለታዳጊዎች ዕድል የሚሰጥ ክለብ በመሆኑ ነው ፡፡ በክለቡ ውስጥ ያለፉ ታዳጊዎች ከግዥ ይልቅ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ፡፡ ይህ ለኢህአዲግ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ካለኝ አድናቆትም ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ኢህአዲግ አገር በቀል ፖሊሲዎች እና ስትራቴጅዎች ቀርፆ በቁርጠኝነት እመተግበሩ በመሆኑ ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ዕድገት በማዝመዝገብ ላይ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ ከእኛ የተለየ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉት ሳይቀሩ የተቀበሉት ነው ፡

ዞወል እስትሬት ጆርናል፣ የፎክስ ኒውስ፣ ስካይ ስፖርት ባለቤት የሆኑት የሩናርት መርደክ ነው ፡፡ ወል እስትሬት ጆርናል ወደ ሪፑብሊካን ፓርቲ ያደላል፡፡ ወደ ኒዮሊብራሊዝም ርዕዮት ዓለም ማለት ነው ፡፡ በአሜሪካን በሥርጭት አድማሱ የመጀመሪያው ሲሆን መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ980,000 ሠዎች በላይ በክፍያ ድረ-ገፁን ይከታተሉታል ፡፡ ጋዜጣው እ.ኤ.አ. ሜይ 15,2014 “why made in Ethiopians could be the next made in China“ በሚል ርዕስ ቶሞ ጋራ የተባለ ፀሐፊ በአንድ ወቅት ቻይና በዓለም ርካሽ ሸሚዝና ካልሲ የሚመረትባት እና የሚገዛባት ሀገር ነበረች ፤ አሁን ግን የጉልበት ዋጋ እየተወደደ ስለመጣ ፋብሪካዎቹ ወደ ቬትናም እና ኢትዮጵያ እየተዛወሩ ነው ፡፡ በዚህም የተነሳ በሚቀጥሉት 1ዐ ዓመታት ሑጃን የተባለው የቻይና የኢንበስትመንት ግሩፕ 2 ቢሊዮን ዶላር እንቨስት አድርጎ ለምዕራብውያን ገበያ ለማቅረብ ዕቅድ እንዳለው አስነብቧል፡፡

ታይም መፅሔት ሚካኤል ሽማን በተባለ ደራሲ እና በኢሲያ ፖለቲካ በኢኮኖሚና ታሪክ የካበተ ልምድ ያለው የመፅሄት የኢሲያ ቢዝነስ ኮርዘስፐንዳንት እ.ኤ.አ.ማርች 13,2014 “Forget the BRICS rneet the PINES” በሚል ርዕስ የፃፈው ፁሑፍ የፊሊፒንስ ፣ የኢንዶኔዥያ ፣ የናይጄሪያና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዴት ከብሪክስ በበለጠ መልኩ እያደገ እንደሆነ አስነብቧል ፡፡ ሚካኤል ሺማን ስለ ኢትዩጵያ ሲገልፅ ኤዢያ ነብር እንዳሏት ሁሉ የአፍሪካ አንበሶች እንደ ኢትዩጵያ ያሉት አስደማሚ ዕድገት እያስመዘገቡ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡

One foot on the ground, One foot in the air Ethiopians agendas” Sept. 2015 በሚል በወጣው ሪፖርት መሠረት የኢትዩጵያ ዕድገት ድሃ ተኮር በመሆኑ ኢትዩጵያ ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል በህዝቦች መካከል እንዲኖር በማድረግ የእነዚህም ዋነኛ መመዘኛዎች አድርጋ የያዘችው ትምህርት ፣ ጤና እና የዕድሜ ጣሪያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ደግሞ የኢትዩጵያ አፈፃፀም ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተቸራቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ፡- የዕድሜ ጣሪያን ከ45 ወደ 64 ለማሳደግ የእናቶችና የሕፃናት ሞት መቀነስ እንዲሁም ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ መሰራቱ ለእድሜ ጣሪያው ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል ፡፡

ሮዝ ያን ደር ያም በአምስተርዳም ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ናቸው ፡፡ እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 22,2015 “Ethiopia should leave Africa“ በሚል ርዕስ በAddis Standard በፃፉት አስደማሚ ፅሑፍ የኢትዮጵያ ዕድገት በተለይም ድህነትን በመቀነስ የሠራችው ሥራ ከጃፓን ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ገልፀው የኢትዩጵያ ዕድገት የአፍሪካን ዕድገትና ልማት ሊመራ እንደሚችል ተስፋቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ሜይል እና ጋርዲያን በዲሴምበር 24,2015 እ.ኤ.አ. “The next 35 Years Nigeria and South Africa may has be Africans begin economies who will? ” በሚል ርዕስ ባወጣው መጣጥፍ እ.ኤ.አ. በ2015 የኢትዮጵያና የኮንጎ ኢኮኖሚ ከናይጄሪያና ከደቡብ አፍሪካ እንደሚበልጥ አስቀምጧል ፡፡ ድህረ-ገፁ አያይዞም እ.ኤ.አ. በ2015 ይህ እድገት ለደቡብ አፍሪካ ፈታኝ እንደሆነ አስቀምጦ ፡፡ እድገቱም ወደፊት የሚቀጥል እንደሆነ ተንብዩአል ፡፡ ለዚህም ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ በማዕድን ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ የማዕድኑ ዋጋ ደግሞ በዓለም ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዋዠቅ በመሆኑ ደ/አፍሪካ አሁን በአህጉሩ ያሉትን የአኮኖሚ መሪነት እንደምታጣ ድህረ-ገፁ ተንብዮአል ፡፡ ፍትሃዊ የሆኑ የሀብት ክፍፍል የሌለበት በመሆኑ አሁን በደ/አፍሪካ ያለው ማኀበራዊ አለመረጋጋት አየተባባሰ ሄዶ የአገሪቱን የኢኮኖሚ መሪነት ሚና ያሳጣታል ፡፡ የሰው ኃይል ስብጥር እና የፋይናንስ ገበያው መዋዠቅም ሌላ ፈተናዎች ናቸው ፡፡ በደ/አፍሪካም ሆነ በናይጄሪያም ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዋዠቅ በመሆኑ እና በዘርፉ ሪፎርም ካስኬደች እሷም በ2015 በኢትዮጵያ እንደምትበለጥ ሜይል እና ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ ድህረ-ገፅ ኢትዩጵያ ግን በ2015 የአፍሪካ ኢኮኖሚ ለመምራት ተስፋ ያላት ሀገር ናት ብሎ አስቀምጧል ፡፡ ስለዚህም ይህ ማሳያ አሁን እያስመዘገብናቸው ያሉትን ኢኮኖሚ ዕድገት እና ልማት በመሠረተ ልማት ማለትም በመንገድ ፣ በባቡር እና በሃይል ፕሮጀክቶች እያደረገች ያለችው ፣ኢንበስትመንቶች፣ ያላት ብቃት ያለው “ቢሮክራሲ” እና መረጋጋት ናቸው ፡፡

Image depicits turn from year 2015 to 2016

ይህንን ያህል ስለ ኢትዩጵያ ካወጋችሁ ዘንድ የፈረንጆች የ2015 ዓመት መጠናቀቅ ተከትሎ በአወንታዊ እና በአሉታዊ መልኩ ዋና-ዋና አስተያየቶችን ታዋቂ ዓለም አቀፍ መሪዎች ንግግርንና የራሴን አስተያየት ለማስቃኘት እሞክራለሁ ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2015 ዓለም የተለያዩ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ ይህንንም በማስመልከት ታዋቂው ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት በዓለም ላይ ከነበሩ ክስተቶች መካከል 10 ዋና-ዋና ዘገባዎችን ለይቶ አቅርቧል፡፡ የሶሪያ ቀውስ መባባስ ፣ የሽብርተኝነት ጥቃት መጨመር ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአውሮፓ የስደተኞች ቁጥር መጨመር ፣ የሩሲያ ጦረኝነት ፣ በአሜሪካ የፖሊስ ፣ ዘረኝነት የጦር መሣሪያ ወንጀሎች እና የማኀበራዊ ዋስትና ፍትሃዊነት መጓደል ጉዳይ ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ፣ ላቲን አሜሪካኖች ግራዘምም ፓርቲዎች ድምፃቸውን የተነፈጉበት በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች ኢኮኖሚ መቀዝቀዝ ፣ የቮልስዋገን የካርቦን ልቀት ቅሌት የፊፋው ፕሬዝዳንት የሙስና ቅሌት በአሉታዊ መልኩ ሲያነሳቸው፤ የኢራን የኒኮሊየር ስምምነት፣ የአሜሪካና የኩባ ግንኙነት ፣ መሻሻል የአሜሪካ ከፍተኛ ጽ/ቤት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ሕጋዊ ማድረግ የዓለም ፖለቲከኞች በአየር ንብረት ለውጥ መስማማት በአዎንታዊ መልኩ ለኢኮኖሚስት አንስቶዋቸዋል፡፡

ዘ ኢኮኖሚስት እንደዘገበው ሽብርተኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ምንም እንኳን የሽበርተኝነት የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ሕጋዊነት የሌላቸው ኢ-ሞራላዊ ቢሆንም በዓለም ላይ የፍትህ መጓደልና ድህነት ዋነኛው ምክንያቶቹ ናቸው ፡፡ ስለዚህ መፍትሄውም ድኀነትንና ኋላቀርነትን ማስወገድ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እና አስተዳደር ማስፈን ነው ፡፡ ኢኮኖሚስትም ሆነ ሌሎች አብኛዎቹ የምዕራባውያን ሚዲያ የሚዘነጉት ነገር ሽብርተኝነት ከሐይማኖት ጋር ማያያዝ ነው ፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም ድርጊቱ ይበልጥ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው ፡፡ ሽብርተኝነት ከየትኛውም ሀይማኖት ጋር መያያዝ የለበትም ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሀይማኖት የሚሰብከው ሠላምን ስለሆነ ነው ፡፡ በተለያዩ ሀይማኖት ያሉ ፅንፈኞች አቋሞች ወደ አሸባሪነት አየተለወጡ እና እየተመጋገቡ መሄድ የዓለም ቁጥር አንድ ስጋት እየሆነ ነው ፡፡የእስልምና አክራሪነት፣ የክርስቲያን አክራሪነትን የክርስቲያን አክራሪነት የእስልምና አክራሪነት በመውለድ የሽብር ጥቃት ለሠላማዊ ሀገሮች እና ዜጎች ሳይቀር እየተረፈ ነው ፡፡ ለዚህ መባባስ የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ እና አልፎ አልፎም ፖለቲከኞች የሚያራምዱት አቋም ለእስልምና አክራሪነት ምቹ ሁኔታዎች እየፈጠረ ነው ፡፡

የዓለም የሠላም እና የኢኮኖሚስ ኢንስቲትዩት “Global Terrorisms index” በሚል በሰጠው ሪፖርት መሠረት ባለፉት 15 ዓመታት የሽበርተኝነት ጥቃቶች እየጨመሩ ነው ፡፡ ኢንስቲትዩት እንደሚለው እ.ኤ.አ በ2014 32,000 ዜጎች በሽበርትኝነት ሕይወታቸውን አጥተዋል ፡፡ ይህ ደግሞ ከ2013 ጋር ሲነፃፀር በ801% ብልጫ እንዳለው ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በጣም አነስተኛው ማለትም 1/5ኛው በምዕራብያውያን ምድር የተከሰተ ሲሆን “በእስልምና አክራሪዎች የተፈፀመው 1/5ኛው ብቻ ነው ፡፡ ኢንስቲትዩቱ አያይዞም በሽብር ጥቃት ከፍተኛ ሞት የተከሰተባቸው ሀገሮች በቅደም ተከተል ኢራቅ ፣ ናይጄሪያ ፣ ፓኪስታንና ሶሪያ ናቸው ፡፡

በምዕራቡ ዓለም የክርስቲያን ፅንፈኝነት ለእስላም ፅንፈኝነት መስፋፋት የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ ነው ፡፡ ታይም መፅሄት እንደዘገበው በአሜሪካ ፀረ ሙስሊም ትዕይንቶች በየጊዜው እየጨመሩ ነው ፡፡ ሙስሊሞች በመንገድ ላይ ይንጓጠጣሉ ፣ ይገደላሉ ወይም እንደሚገደሉ ዛቻ ይደርስባቸዋል ፡፡ መስጊዳቸው ላይ እና በንግድ ተቋማት ላይ ጥቃቶች ይሠናዘራሉ ፡፡ ታይም እንደሚለው በየወሩ በአማካይ 12.6 በመቶ የጥላቻ ጥቃት በሙሲሊሞች ሲደርስ የነበረው ከፓሪስ ጥቃት በኋላ በ3 እጥፎች አድጓል፡፡ እነዚህ ጥቃቶች ደግሞ ለአሸባሪው ISIS ገንዘብ እንደመለገስ ነው ፡፡ እጅግ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ እነዚህ ትዕይንቶች በፖለቲከኞች ንግግር ሲደገፉ ነው ፡፡ ኦባማ ሙስሊም ነው ፣ አሜሪካን ማስተዳደር አይገባውም የሚሉ ፖለቲከኞች ብዙ ናቸው ፡፡ ባለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማት ሮሚኒ የተባሉ ተወዳዳሪ የምርሞኒዝም ሀይማኖት ተከታይ በመሆናቸው ብቻ በመጀመሪያ ያገኙት ተቀባይነት በከፍተኛ ሁኔታ ተሽርሽሮ ነበር ፡፡ ሜሼል ፔሪ የተባለች ተወዳዳሪም እሷ ፕሬዚዳንት ከሆነች በአሜሪካ የግብር ምጣኔ ከመፅሐፍ ቅዱስ ተወስዶ 10 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ቃል ገብታ ነበር ፡፡ በተመሳሳይ በዘንድሮው የፕሬዚዳንት ፉክክር የሪፓብሊካኑ ዶላንድ ቱርብ አሸባሪነትን ለመከላከል ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ መከልከል መፍትሔ ነው ይላሉ ፡፡ ይህ ንግግራቸው በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ከብዙ ሀገሮች ተቃውሞ ገጥሞታል ፡፡ እንግሊዝ ውስጥ መግባት እንዳይችሉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ፊርማ ተሰባስቧል ፡፡ ይህ አባባላቸው የአሜሪካን ህገ መንግሥት እና መሠረታዊ እሴቶችን የጣሰ ከሀይማኖት ጋር ምንም የማይገናኝ በማለት በፅኑ የተቿቸውም አሉ ፡፡

በእርግጥም ትረምፕ ጥላቻቸው በሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን በጥቁሮች በአካል ጉዳተኞች በሜክስኬያውያን ጭምርም ነው፡፡ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ በምዕራቡ ዓለም እየተስፋፋ የመጣው ዘረኝነት ብዝሃነትን ለመቀበል ስላዳገተው ለሽበርተኝነት መስፋፋት ከፍተኛውን አስተዋፅኦ እያደረገ ነው ፡፡ ይህ ደግሞ ለሀገራችንም ሆነ ለጎረቤቶቻችንም የሚተርፍ ነው ፡፡ በቅርቡ ሲ.ሲ.ቲቢ. እንደዘገበው ISIS ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው ምሥራቅ አፍሪካ እንደምትሆን አስቀምጧል ፡፡ ስለዚህ ልዩነታችንን ወደ ጎን በመተው ለሀገራችን ህልውና በጋራ መቆም ከመቼዉም ጊዜ የበለጠ ትኩረት ሊንሰጠው የሚገባን ስራችን ነው ፡፡

በ2015 ዋነኛ ሁነቶች መካከል ዓለም የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በፖሪስ የደረሱበት ስምምነት ነው ፡፡ በስምምነቱ 195 ሀገሮች የዓለም የሙቀት መጠን ከ1.5 በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት ተስማምተዋል ፡፡ ይህ ማለት የሙቀት መጠኑ ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ባለበት ደረጃ እንዲሆን የሚያስችል ነው ፡፡ ሀገሮች የተለያዩ የዕድገት ደረጃ ላይ መገኘታቸው የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረሱ አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል ፡፡ በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው ጥርጣሬም እንቅፋት ነበር ፡፡

ባለሙያዎች እንደሚሉት የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተራሮች እየተንሸራተቱ ነው ፡፡ የባህር ወለል ከፍታ እየጨመረ ነው ፤ ከባድ የድርቅ ጉዳት እና ጎርፍ እየተከሰተ ነው ፡፡ ይህ ደግሞ መፍትሔ ካልተበጀለት ወደ ውድቀት አለም እያመራች ነው ፡፡ በፓሪስ የተደረገውን ስምምነት የዘርፉ ባለሙያዎች አወድሰውታል ፡፡ ቢሆንም ግን አሁንም በአተገባበሩ ዙሪያ ሥጋቶች ያሉ መሆኑ ፡፡ ስምምነቱ ወደ የሀገራት ሕግ አውጭም ም/ቤት ለማፀደቅ ሲቀርብ ለተለያዩ ትርጉምና አስተያየቶች ምላሾች ሊደረግ ይችላል ፡፡

በተለይም የአሜሪካ ኮንግረስ ማሳመን እጅግ ከባድ ነው ፡፡ በተለይም ሪፓብሊኮኖችን ይላሉ ፡፡ ተቺዎች የአሜሪካን ሪፑብሊካን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባላቸው አቋምና ዳይኖሰርስ የጠፋው በአየር ንብረቱ ለውጥ አይደለም ብለው ያምናሉ ስለ፤ዚህ ከባድ ይሆናል ይላሉ ፡፡ በፓሪሱ ስምምነት መሠረት የበለፀጉ ሀገራት በማደግ ላይ ላሉት ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ለአየር ንብረቱ ለውጥ መቋቋሚያ ለመስጠት ተስማምተዋል ፡፡ በአመቱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል ፡፡ የተጠያቂነትም አሠራር ተዘርግቷል ፡፡ ሁሉም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በቋሚነት ሪፖርት እንዲያቀርቡ ስምምነቱ ያስገድዳል ፡፡ ለስምምነቱ የኢትዮጵያ አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነበር ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ ሀገራት እርሙን ለመሙላት ኢትዮጵያ በፐሬዚዳንትነት ተመርጣለች፡፡

*************

* ስንታየሁ ግርማ – የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

Guest Author

more recommended stories