የISIS/ISIL የኢትዮጲያውያን ግድያ ቪዲዮ ምን ይላል?

IS ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አለም-ዓቀፍ አሸባር ቡድን አል ፉርቃን በተባለ ሚዲያ በኩል “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮችን” በአረመኔያዊ አኳኋን የገደለበትን ቪዲዮ መልቀቁ ይታወሳል፡፡ ቪዲዮውን መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦች፡-

* ነሳራ (Christians/The people of the book)

* ኢብን ቴይሚያ (Ibn Teymiyyah)

* ጂዝያ (ያላመኑ ላይ የሚጣል ግብር)

* የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች (The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt))

ይሀ ቪዲዮ የ29 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን በጥቅሉ በነሳራ/በክርስትያኖች (The people of the book) ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በዚህም ነሳራን በአራት ክፍሎች ያስቀምጣል፡፡Photo - Islamic State beheads of Ethiopian Christians in Libya

1/Western Catholic Church (Europe & other Eastern countries).

2/ The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt).

3/ The Eastern Orthodox Church (Russia, Greece, Many Mediterranean states).

4/ The Protestant Church (Germany, America, Scotland, Norway and Holland)

ከዚህ ቪዲዮ አላማ አንፃር ሲታይ ይህ ቪዲዮ ያነጣጣረው የኢትዮጵያና ግብጽ የጋራ መለያ በሆነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

ለዚህም ነው የግድያውን ምክንያት “ጠላት የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን መስቀል ተከታዮች” በማለት የገለፀው፡፡

ከ22፡30 – 23፡40 ባሉት ደቂቃዎች ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች ሁለት (2) መሰረታዊ መልዕክት ያላቸውን ለማስተላለፍ የሞከረው፡፡ እነኝህም፡

1/የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓትን እስልምናን በመቀበል እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡ

2/ ከባርነት ወደ ነጻነት እንዲሸጋገሩ – አንድ ግዛትና አንድ መሪን በመቀበል

ከ24፡00 – 24፡20 ባሉት ደቂቃዎች ከተያዙት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ተከታዮች ውስጥ ሶስቱ (3) በIS እስልምናን በመቀበል የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓት መቀላቀላቸውን ያሳያል፡፡

በቪዲዮ መሰረት የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓት በሸሪዓ ህግ የሚተዳደር መሆኑን ይገልጻል፡፡ በዚህም አ-አማኒዎች ላይ የሚጣል ግብር (ጂዝያ) እንደሚያስከፍል ይናገራል፡፡ የክፍያ ተመኑንም እንዲህ አስቀምጦታል፡፡

* በወርቅ ማንጠርና ማብላላት ላይ ለተሰማሩ – – – አራት ዲናር (4 Dinar) / 4.58ዲናር = 232ብር

* ከወርቅ ማንጠርና ማብላላት ውጭ ስራ ላይ ለተሰማሩ – – – አርባ ድርሃም (40 Dirham) / 40.17ድርሀም = 6.8ብር

የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) በአገዛዙ ውስጥ የሚኖሩ እስልምናን ያልተቀላቀሉ ግለሰቦችን በምቾትና በተሻለ ደረጃ እንደሚኖሩ ለማሳየት ጥሯል፡፡ በዚህም ወደ አራት የሚሆኑ ግለሰቦችን ቃለመጠይቅ አዘል ማስታዋቂያ በቪዲዮ ውስጥ አካቷል፡፡

የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አንድ ግዛትን በሚቆጣጠርበት ወቅት የሚያደርጋቸውን ተግባራቶች ማለትም የቤተ ክርስትያን ሃይማኖታዊ ምልዕክቶችን፡ ስዕላትን፡ መስቀላትን በመሰባበርና በማውረድ በፋንታው የራሱን ጥቁር ባንድራ ሲተክል ይታያል፡፡ ይህንንም በቪዲዮ ውስጥ አሳይቷል፡፡

ከቪዲዮው በመነሳት የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓትን እንዲህ ማስቀመጥ ይቻላል:-

1/ እስልምናን በመቀበል እንደ – አንደኛ አማራጭ

2/ እስልምናን ካልተቀበሉ በተመኑ መሰረት አስፈላጊውን ጂዝያ በመክፈል በሰላም መኖር – እንደ ሁለተኛ አማራጭ

3/ ሁለቱንም አማራጭ ካልተቀበሉ የሴይፍ ሰለባ መሆንን – እንደ ሶስተኛ አማራጭ

ከሃይማኖታዊ ይዘት አንጻር:-

ኢስላሚክ ኢስቴት (IS) ከዚህ በፊት እንደሚያደርግ ሁሉ በዚህ ቪዲዮም ውስጥ የተጠቀመባቸው የቅዱስ ቁርዓን ዓየቶች (አንቀጾች) እና ሐዲሶች ለዘመነ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አካባቢ ለነበሩ ጦርነቶች የሚያገለግሉና ለጦርነቱ ወቅት የወረዱ ሲሆን ከፊትና ከኋላ የቀነጫጨበበት እና ትርጉሙን የሳተ ነው፡፡

ኢስላሚክ ኢስቴት(Islamic State) በዚህ ቪዲዮም እንደ ፈትዋ (ዉሳኔ ለመወሰን የተከተለው) የተጠቀመው ኢብን ቴይሚያ (Ibn Teymiyyah)፡ አብሮ አደጉ አወዛጋቢው ፈላስፋና የስነ-ልቦና ጠቢብ ኢብኑል ቀይም (Ibnul Qeyyim) እና የሻም ሊቁ የሐንበሊ ፊቅህ ፈላስፋ ኢብን ቁዳማሕ አል-መቅደስይን (Ibn Qudamah Al-Muqadasiy) ነው፡፡

ይህ ኢስላሚክ ኢስቴት እንደ ፈትዋ የተጠቀመው ኢብን ቴይሚያ (Ibn Teymiyyah) የመካከለኛው ዘመን ሊቅ፡ ፈላስፋ እና ተዋቂ ፖሎቲከኛ የነበረ ሲሆን የሐንበሊ መዝሀብ (Hanbali Sect) ዋና አቀንቃኝና የጂሃዲዝምና ዋሃቢዝም ዶክትሪን ፈላስፋ ነው፡፡

በኢብን ቴይሚያ አስተምህሮት ሰለባ ከሆኑት ውስጥ የሙስሊም ወነድማሞች መስራች ግብፃዊው ሐሰን አል ባኒ (Hassen Al-Bani)፡ ተዋቂው የሙስሊም ወነድማሞች አንቀሳቃሽና የንድፈ-ሀሳብ ሊቅ ሠይድ አል ቁጥብ (Seyid Al-Qutub) እና የኢብነ ሰዑድ ንጉሳዊ ግዛት (የሳዑዲ ዓረቢያ ንጉሳዊ ቤተሰብ) አና የወሀቢያ አስተምህሮትና እንቅስቃሴ መሰራች የነጅዱ ተወላጅ መሐመድ ኢብን አብደል-ወሃብ (Mohammed Ibn Abdal-Wahab) ይገኙበታል፡፡

********

Abdulbasit Abdusemed

more recommended stories