ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግል 10 ዓመታ ካስቆጠረ በኋላ፤ በ1977ዎቹ የፖለቲካ አመራር የሚሰጥ አደረጃጀት ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግPhoto- General Tsadkan and Daniel-Berhane ትግራይ(ማሌሊት) በሚል ስያሜ እንደመሠረተ ይታወሳል፡፡

ያ አደረጃጀት ዓለም-አቀፋዊውን የአሰላለፍ ለውጥ ተከትሎ ከ1983 በኋላ እንዲቀር መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአብዛኛው ሕዝብ እምብዛም አይታወቅም፡፡

ይሁን እንጂ ህወሓት ከ1970ዎቹ አጋማሽ በኋላ ላሳየው የወታደራዊ እና ድርጅታዊ እመርታ ምክንያቱ የማሌሊት ምሥረታ ያስከተለው የርዕዮተ-ዓለም ጥራት ነው ብሎ ያምናል፡፡ በአንጻሩ የቀድሞው የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ የተገኙት ለውጦች ያለማሌሊት ሊከሰቱ የሚችሉ የአደረጃጀት ለውጥ ውጤቶች ናቸው የሚል ሀሳብ አንስተዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ቃለ-መጠይቅ ያደረግንላቸው ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሰኤ ካቀረብነው ጥያቄዎች አንዱ ማሌሊትን የተመለከተ ነበር፡፡

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት እና ማሌሊት ሲቋቋም ከመጀመሪያዎቹ 9 የፖሊት ቢሮ አባላት አንዱ የነበሩት እንዲሁም የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጻድቃን፤

* የማሌሊት ምሥረታን እና በሕወሓት መዋቅር ላይ የነበረውን ፋይዳ ያብራሩ ሲሆን አያይዘውም

* የህወሓትን ወታደራዊ ስትራቴጂ ጽንሰ-ሀሳቦች፣

* ከደርግ 603ኛ ኮር ጋር በሽረ የተደረገውን ውጊያና ተዛማጅ ታሪካዊ ሁነቶችን እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡

[እስከ 1993 የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም የነበሩት ሌፍተናንት ጄኔራል ጻድቃን፤ የህወሓት-ሻዕቢያ ግንኙነት፣ የ1977ቱ ረሀብ፣ በኤርትራ ወረራ ወቅት የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሚና፣ የቀድሞው ሠራዊት መበተን እና ሌሎች ዐብይ ርዕሰ-ጉዳዮች እንዲሁም ስለራሳቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሾች በተከታታይ እናቀርባለን]

——

Watch Video below.

 

*************

Daniel Berhane

more recommended stories