የአንድነት የቀድሞ ፕ/ት ኢ/ር ግዛቸው:- ‹‹ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው››

የአንድነት ለዴሞክራሲ እና  ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፍራው የአንድነት አባለት ለፓርቲው ህልውና ሲሉ የተፈጠረውን ችግር በሰከነ መንፈስ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ::

የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ በሚመራው ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት ግርማ ሰይፉ በኩል ከፓርቲው  መሪነት የተነሱት ፓርቲውን የመምራት እና ጫናን የመቋቋም አቅም ስላልቻሉ ነው መባላቸውን በታህሳሱ ምርጫ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር አቶ ግርማን  በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ማሸናፋቸውን በማንሳት ኃሳቡን አጣጥለውታል።

በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ቀን ተሸናፊው አቶ ግርማ ራሴን ያየሁበት ውድድር ነው።

ውጤቱም እንኳንስ ፓርቲ ወረዳ  መምራት የማልችል መሆኔን የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ያስታወሱት ኢንጅነር ግዛቸው ስልጣኔን ያስረከብኩት ፓርቲው በቡድን ፓለቲካ እንዳይፈርስ ለህልውናው በማሰብ ነው ብለዋል።

አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚል አስተያየት የሰነዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን መፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት የከፈሉት አመራሮች ችግራቸውን በጋራ በውይይት እንዲፈቱ የሁለት ሳምንት ግዜ መስጠቱ ይታወሳል።

*********

ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 09-2007

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories