ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በጋራ ግድብ ለመገንባት ተስማሙ፡፡

ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በዳዋ ወንዝ ላይ ሁለንተናዊ ግልጋሎት የሚሰጥ ግድብ እና የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያመነጭ ግድብ ለመገንባት ተስማሙ፡፡Genale Dawa River Basin

ሀገራቱ ኢትዮጵያን ከኬኒያ የሚያገናኝና አካባቢያዊ ልማቶችን የሚያፋጥን ድልድይ ለመስራትም ተስማምተዋል፡፡

ሀገራቱ ስምምነቱን የፈረሙት በአፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት /ኢጋድ / አደራዳሪነት ነው፡፡

በወንዙ የጋራ አስተዳዳሪነት ትብብር ዙሪያም በኬኒያ ናይሮቢ በተካሄደው ውይይት ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ሀገራቱ በፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ዙሪያ በጋራ የሚሰራና ከሁሉም ሀገራት የተወጣጣ ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ኬንያን የወከሉት የማንድራ አገረ ገዢ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ሀብትን ለዘላቂ ልማት በማዋል ዜጎች በቀጠናው የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡ ያስችላል ።

ኢጋድ በስምምነቱ መሰረት ፕሮጀክቱን በበላይነት እንዲመራ ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

የዳዋ ወንዝ በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኝና ኬኒያንና ሶማሊያን የሚያካልል ለ9 ወራት የሚስ ወንዝ ነው፡፡

********

ምንጭ፡- ከኢቢሲ [ከስታንዳርድ ዲጅታል ኒውስ የተተረጎመ] – ሕዳር 6፣ 2017

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

more recommended stories