በኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የተፈጠረውን ሁከት የሚያወግዝ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የተፈጠረውን ሁከት የሚያወግዝ ሰልፍ እዚያው ከተማ ተካሄደ፡፡ EthiopianEmbassyWashington DC

ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጥቂት የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመግባት፣ “አምባሳደሩን እንፈልገዋለን” ሌባ ባንዳ ወዘተ በማለት ረብሻ ከማስነሳታቸው በተጨማሪ የኢትዮጲያን ባንዲራ በማውረድ እና አንድ የኤምባሲውን ቢሮ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመያዝ ከፍተኛ ግርግር መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ ግለሰቦቹን ለመከላከል የሞከረ አንድ ዲፕሎማት ጥይት መተኮሱ እና ለጥቆም ወደሀገር ቤት መመለሱ አይዘነጋም፡፡

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት ‹‹ኢትዮጲያውያን ለሰላም›› በማለት ራሳቸውን የሚጠሩ ሰልፈኞች ድርጊቱን ተሰምቶ የማይታወቅ እና ክብረ-ነክ ነው በማለት አውግዘዋል፡፡

ሰልፈኞቹ አክለውም ሁከት ፈጣሪዎቹ ኤምባሲውን እስከመያዝ መድረስ መቻል አልነበረባቸውም፡፡ በዚህም ሳቢያ የአሜሪካየውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እና የዲፕሎማሲ ጥበቃ ሀይሉ() ሀላፊነታቸውን በበቂ እንዳልተወጡ ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

ግርግሩ ከተፈጠረ በኋላ መግለጫ የሰጡት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩ፤ ግለሰቦቹ ቁጥራቸው ከ10 እስከ 15 የሚጠጋ እንደነበር እና ለአንድ ሰዓት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ማንነታቸውን በመለየትና አድራሻቸውን በመያዝ እንዲለቀቁ መደረጉን አምባሳደር ግርማ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ አክለውም፡- በእለቱ ምንም ዓይነት በህጋዊነት የተጠራ ሰልፍ እንዳልነበር፣ ‹‹የድርጊቱ ፈፃሚዎች በየቦታው በሚዘጋጁ ሰልፎች ሁሌም በሁከት መልክ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ለስራ ወደ አገሪቱ ሲመጡ እየተከታተሉ ተራና የወረደ ስድብ የሚሳደቡ በተወሰነ የፖለቲካ ድርጅቶችና በሻእቢያ ጀሌዎች የሚነዱ›› ናቸው ማለታቸው ይታወሳል፡፡
********

Daniel Berhane

more recommended stories