ሬድዋን ሁሴን:- የአሜሪካው ተቃውሞ ‹የወረደ ስብዕናን ያመለክታል›፣ ‹ከሕግ አንፃር በዝርዝር ይታያል› [Transcript]

በአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች የንግድ ፎረም ላይ ለመሳተፍ እና ጎን ለጎን በተዘጋጁ የተለያዩ መድኮች ላይ ለመገኘት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን ያካተተ የልኡካን ቡድን ወደ አሜሪካ ባለፈው ወር መሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት የዲያስፖራው አባላት ተቃውሞዎች አካሄደዋል፡፡ ከነዚህም መሀል፣ በነሐሴ 2/2006 ዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኝ – አርሊነግተን በተሰኘች – ከተማ ውስጥ ወደ አንድ የገበያ ማዕከል በሄዱበት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ላይ ሁለት ጽንፈኛ ዲያስፖራዎች ዘለፋ፣ ዛቻ እና ሁከት መፈፀማቸው እና ሁኔታውንም በሞባይል ቪዲዮ ቀርፀው ማሠራጨታቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ጉዳይ በዚህ ሳምንት ሰኞ ነሐሴ 12/2006 አቶ ሬድዋን ሁሴን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነስቶ ነበር፡፡ አንድ ጋዜጠኛ – ክስተቱ ከኢትዮጲያዊ ጨዋነት ጋር አብሮ ይሄዳል ወይ? ህገወጥ አይደለም ወይ? እስከመቼ ነው መንግስት በዝምታ የሚያየው? የሚል ይዘት ያለው ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፤ አቶ ሬድዋን ሁሴን ሰፋ ባለ መልኩ በሌሎች ቦታዎች የተደረጉ ተቃውሞዎችን አካትተው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የአቶ ሬድዋን ሁሴንን መልስ እንደወረደ በጽሑፍ (transcribe በማድረግ) አቅርበነዋል፡፡

[በመግለጫው በተነሱት ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦችን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ለማንበብ ይህን (link) ይጫኑ፡፡]

በሂውስተንም ካለፎርኒያም መድረክ ነበር፡፡ በዲሲ የነበረው የመሪዎች ስብሰባ ነው ፡ የተለየ የኢትዮጲያ መድረክ አልነበረም፡፡

ቴክሳስ የነበረውን ካየን በጣም በርካታ በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩ ትልልቅ የዲያስፖራ አባላት ኢትዮጵያውያን የነበሩበት ሲሆን በሂውስተን የነበረውን መድረክ ያዘጋጁት (አዛ የክብር ቆንስል እንጂ ቆንስላ ስሌለን) Yale ያሉት ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከስምንት ወር በላይ እየተሰበሰቡ ገንዘባቸውን አውጥተው ከተከፋይ የኤምባሲ ሠራተኞቻችን በላይ ያሳኩት ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ የሚሰሩ ሀገራቸውን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ዜጎች አሉ፡፡

በዛ በመድረክ አካባቢ በአንድ በኩል አገራቸውን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እያሉ 18 የሚሆኑ መድረኩን የሚቃወሙ ሰዎች አይቻለሁ፡፡ የፌስቡክና ትዊተር አካውንቴን ካያችሁት በjuly ለጥፌዋለው ፡ በዝርዝር ይታዩ ስለነበር ማለቴ ነው ፡ ሆቴሉ አካባቢ ላይ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ሂውስተን አካባቢ የነበሩት ቁጥራቸው ትንሽ ነው ፡ በርከት ያሉት ከዳላስ የመጡ ነበሩ ፡ የአካባቢው እዛ ያሉ ሰዎች እንደገለፁልን ከሆነ፡፡

ሁለተኛው መድረክ የካሊፎርኒያው ነው፡፡ ሎስአንጀለስ የነበረውን ካያችሁ እዛ አዳራሽ የነበረውን ሰው በዝርዝር ለማየት ተሞክሩዋል ፡ እንደዚሁም በጊዜው በፌስቡክም በትዊተርም ተላልፍዋል፡፡ በEBS ላይም ማታ ሄዶል አትሊትስ ፕሮግራም ላይ ያለውን ሰው በስፋት ታይቶላችሁ፡፡ ይሄ ሰው በቂ አዳራሽ ስላልነበረን ተበትኖ ነው የገባው፡፡ አልተነገረንም፡ መነገር ነበረበት፡ መግባት አለብኝ የሚሉ ሰዎች በጣም በርካት ነበሩ፡፡ ቦታ መመጠን ስላስፈለገ የተወሰኑት ገብተዋል፡፡

እዛ አካባቢ የነበሩ ህገወጥ ተቆጥረዋል፡ ቢያንስ ሆቴላችን አካባቢ ስለነበሩ ከ15ኛ ፎቅ ለመቅረፅ ተሞክሮዋል፡ 30 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡

ስለዚህ በአንድ በኩል አዳራሽ እየሞላ የሚከታከት ለሀገሬ ምን ልስራ የሚል አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ መፈክራቸውንም ከሰማችሁት የሚሳደቡት አመራርንም አይደለም ባለሃብቶቹን ነው፡፡

ከዚህ ሀገር የተሳካላቸው ሰዎችን ኑሮዋቸውን ሃብታቸውን አፍርተው ልክ እንደኛ ኢትዮጵያ ውስጥ መጥታችሁ ሀብት ማፍራት አለባችሁ ለማለት የሚሄዱ የነበሩ ሰዎችን ባንዳ እያሉ ነበር የነበሩት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ አመራር መሆን የፖለቲካ ልዩነት ይሆናል፡፡ ዜጎች ሀብት አፍርተው ሌሎች የሀገር ዜጎችን ኑና ሀብት አፍሩ ከእኛ ጋር መጥታችሁ እንደኛ ስሩ ነግዱ አትርፉ ማለት ባንዳ የሚያሰኝ አቋም የሚያስወስደው ሰው ምን አይነት ሰው ነው? የሚፈልጋት ኢትዮጵያ ምን አይነት ኢትዮጵያ ናት? የሚል ጥያቄ ማንሳት ይችላል፡፡ ደግነቱ ከዚያ ሁሉ ፡ 320 ሰው በአንድ አዳራሽ 30 ሰው በሌላ ጫፍ ነው ያለው ማለት ነው፡፡

በዲሲ ያለውን ካያችሁ ዲሲ ስንት ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንዳለ መውሰድ ይቻላል፡፡ 700,000ም ከዛ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ 200 ሰዎች ነበሩ ሰልፍ የሚያደርጉም ሆነ የሚሳደቡ የነበሩት፡፡ እሱም በአጠቃላይ ሊወሰድ ይችላል ድምሩን ከወሰዳችሁት፡፡ እና ከአጠቃላይ ዲያፖራው ካየነው በሀገር ውስጥ ስላለው እንቅስቃሴ መረጃም አለው እየወጣም ይሄዳል ቢያንስ በኦንላይን ሚዲያዎችም ሆነ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚያገኛቸውን መረጃዎች ይወስዳል፤ እየሆነ ባለው ነገር ደስተኛ ነው፡፡ አሁን አሁን እንደውም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እድገት ከኢትዮጵያ መንግስትና ሚዲያዎች ከሚገኘው ባሻገር በጣም በበርካታ ሚድያዎችና ተቋማት እውቅና የተሰጠው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይበልጥ እየተደሰተና እየኮራ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የተለየ ሌላ ፅንፈኛ ወገን አለ፡ ጥቂት ነው፡ ይሄ ጥቂት ሀይል አይኖርም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡ በየትኛውም ግዜ ይኖራል፡፡ እንዳይኖር ማድረግም ከንቱ ልፋት ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው፡ በጣም ጠርዝ ይዞ የሚንቀሳቀሱ አባላት ይኖራሉ፡፡ ምን ያህል ሰው ያንቀሳቅሳሉ ለሚለው፡ ብዙሀኑ ደስተኛ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑት ከ200 ምናምን ሰልፈኞች ባሻገር በግለሰብ ደረጃ መጥተው የሚተናኮሉት ካየናቸው፡ እንደነዚህ አይነት የሚጮሁት ሁለት ሶስት ባሉበት አካባቢ ሃያ ሰላሳ ሌላ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ያ ሰው ወይ ይረግማቸዋል ወይ ጠርዝ ይዞ ቆሞ ይታዘባቸዋል፡ ግን አብሮዋቸው አይደለም ያለው፡፡ ስለዚህ ያን መውሰድ ከቻልን ያብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ አቋምን አይመለከትም፡ የእነሱን ልብም አልገዙም፡ የተነጠሉ በመነጠል ላይ ያሉ አጀንዳቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውም የተናጥል የሆነበት እና ተስፋ መቁረጥ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ላይ ነው ያለው እና ዲያፖራውንም አይመለከትምም አይወክልምም ብሎ መውሰድ ይችላል፡፡

ከህግ አንፃር ያለው በዝርዝር ይታይ እና ያው እንደተባለው personal threat (ግለሰብ ላይ ዛቻ) አይፈቅድም ግን መፈክር ማሰማት ይችላል፡፡ ዋናው ከዚህ የሚወሰደው የእነዚህ ሰዎች ስብእና ምን ድረስ ወርዷል የሚለው ነው፡፡

ይህንን መውሰድ ከቻልን ምን አይነት የፖለቲካ አመለካከት ይወክላሉ የሚለውን፡ ምንም አይነት የፖለቲካ አመለካከትን አይወክሉም፡ የወረደ ስብእናን ይወክላሉ፡፡ ከዚህ አንፃር አጠቃላይ ህዝቡ እንዴት ሊመክታቸው ይችላል የሚለውን መውሰድ ነው የሚሆነው፡ የቀረው ራሱን ተከትሎ ስለሚሄድ በዛው ይሄዳል አመሰግናለሁ፡፡

**********

**********

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

more recommended stories