የሰሞኑ የመርሃ-ቤቴ ዓለም-ከተማ የሁከት ሙከራና እውነታው

በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሃ ቤቴ ወረዳ ዓለምከተማ ሰሞኑን በፅንፈኛ ተቃዋሚው አፍ ውስጥ ገብታለች፡፡

አንዱ የፅንፈኛ ዲያስፖራ ተቃዋሚ ድረ ገፅ “ቁስለኞች ሆስፒታሉን አጣብውታል። ቁስለኞቹ የሚታከሙት በፖሊስ ታጅበው ሲሆን ህክምናውን እንደጨረሱ ወደ እስር ቤት ይወሰዳሉ።” ሲለን፤ ሌላው ሀገር ውስጥ ያለ ደጋፊው ይነሳና ደግሞ “የሰሜን ሸዋን የመራቤቴን የእምቢተኝነት መንፈስ መላው የአማራ ህዝብ ሊላበሰው ይገባል” ይለናል፡፡Alem Ketema town - Merhabete woreda - Amhara Region - Ethiopia

ሌላው ደግሞ “ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል። ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን ሙሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል።” ይልና “እባካችሁ እዛ ያላችሁ ታጋዮች መረጃ አድርሱን” ይላል፡፡ ያለመረጃ እየፃፈ መሆኑን እያሳበቀ መሆኑን ግን አያስተውልም፡፡

እኔ ግን መረጃውን ከገለልተኛና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጭምር አጣርቻለሁ፡፡ የማይመለከታቸውን ተስፈኛ ተቃዋሚዎችን ለማነጋገር ያደረግሁት ጥረት ግን የለም፡፡ 

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ 12 አካባቢዎች መብራት ከሰኔ 29 ቀን ጀምሮ ተቋርጦባቸው ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአካባቢው የነበረ ትራንስፎርመር መቃጠሉ ነው፡፡ መብራት ሀይል በእንዲህ አይነት ወቅት የሚወስደው እርምጃ ሁለት ነው፡፡ አንድም ቶሎ አዲስ ገዝቶ ማቅረብና ችግሩን በዘላቂነት መፍታት፤ አለዚያም በአቅራቢያ በትርፍነት ካለበት ቦታ በማዘዋወር መፍትሄ ማበጀት፡፡ በርግጥ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆንም ሶስተኛ አማራጭ መሆኑን እሱ ባያምንም እኛ ደርሰንበታል፡፡

ለዚህኛው ችግር ተቋሙ የመረጠው መፍትሄ ከሌላ አቅራቢያ ቦታ ከተቀመጠ ትራንስፎርመር አምጥቶ ችግሩን መፍታት ነው፡፡ ለዚህም በቅርብ ከሚገኘው መርሃቤቴ ወረዳ ዓለምከተማ ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ ያልሆነ ያይደለ ትራንስፎርመር ተመራጭ ሆነ፡፡

በዚሁ መሰረት የመብራት ሃይል ቴክኒሻኖች ወደከተማዋ በመሄድ በከተማዋ ዳር ከሚገኘው ማሰራጫ ጣቢያቸው ግቢ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ለጭነት በሚመች መልኩ መፍታት ጀመሩ፡፡ ይሄኔ አንዱ የዛ መስሪያ ቤት ባልደረባ በብርሃን ፍጥነት ወደ ከተማ በመግባት ለነዋሪዎቹ ‹‹ተዘረፋችሁ›› ይላል፡፡

ይህችን እሳት ያገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎች ደግሞ ምን አይነት ቤንዚን መርጨት እንዳለባቸው አላጡትም፡፡ <<ትራንስፎርመርህ ተነቅሎ ወደትግራይ ሊጋዝ ነው>> ሲሉ የቤት ለቤት ቅስቀሳቸውን አጧጧፉት፡፡ የመንጌን ንግግር በመዋስ <<ተንቀናል፤ ተዋርደናል፤ በቁማችን ገድለውናል>> እያሉም ከተማዋን በአንድ እግሯ አቆሟት፡፡

የመብራት አቅርቦቱ ሊዳፈንበት የመሰለው የዓለምከተማ ነዋሪም በተሰጠው የሀሰት መረጃ ተወናብዶ መቆጣት ጀመረ፡፡ <<ለምን ተብሎ?>> ሲልም ጥያቄውን አነሳ፡፡ <<አይ፤ የከተማው መብራት አይቋረጥም>> ያሉትንም ሊሰማቸው አልፈቀደም፡፡

የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ለሁለት ጊዜያት አካባቢውን ጎብኝተው ነበር፡፡ ያኔ ነዋሪውን ሲያነጋግሩ ከቀረቡላቸው አቤቱታዎች ውስጥ አንዱ የመብራት አቅርቦት ችግር ነበር፡፡ አሁን በከተማዋ ያለው ሰብሰቴሽን(substation) ከሳቸው የቀጥታ አመራር ጋር የተያያዘ ታሪክ ያለው ነው፡፡

<<ታዲያ ከተማችን እያደገች፤ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እየተበራከቱ፤ የሃይል ፍላጎታችንም አይጨመረ ባለበት፤ ሁሉም የገጠር ቀበሌዎቻችን የመብራት ተደራሽ ባልሆኑበት ሁኔታ ለምን ትራንስፎርመሩ ይወሰዳል?>> ሲል ቁጣውን አከረረ፡፡ ተቆጥቶም ዝም አላለ፤ ተሰባስቦ ከተማዋ ዳር ወዳለው ማሰራጫ ጣቢያ ሄደ፡፡

በወቅቱ አገር ሰላም ብለው ስራቸውን ያከናውኑ የነበሩ ባለሙያዎች ድንገት የወረራቸውን የመሬ ሰዎች ሲያዩ ሳይደነግጡ አልቀሩም፡፡ ያው መሬ፤ መንዜ የሚባሉ አካባቢዎች ያላቸውን ዝና የምታውቁት ነው፡፡ ባለሙያዎቹ የህዝቡን ጥያቄ ተቀብለው ስራቸውን አቆሙ፤ ለህዝቡም ይህ አይነት ያለመግባባት ባለበት ሁኔታ ትራንስፎርመሩን እንደማይወስዱት ነግረው ህዝቡን ወደቤቱ መለሱት፡፡

ይሄ ውዠንብር ብቻውን ለተቃዋሚዎች የረባ ትርፍ የሚያስገኝላቸው አይሆንም ነበረ፡፡ ምክንያቱም በሰከነ አዕምሮ ውይይት እንደሚካሄድበትና ያኔ የሃሰት ካባቸውን ተገፈው ራቁታቸውን እንደሚቀሩ ያውቁታልና፡፡ ስለሆነም በፍጥነት ዘየዱ፡፡ በዚህ ነገር የሰው ደም መፍሰስ አለበት የሚል፡፡ ለዚህ ደግሞ ህዝቡ አርፎ ቤቱ እንዳይቀመጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እናም ህዝቡን ለሊት ሳይቀር ቤቱ እየሄዱ አንተ ስትመለስ ሊጭኑት ተስማምተዋል ይሉት ጀመር፡፡ ጎን ለጎንም ባደራጇቸው ህገወጦች አማካኝነት በለሊት እንደ መብራት ሃይል፤ ኢትዮ ቴሌኮም፤ አበቁተ እና መሰል ተቋሞችን በድንጋይ በማስደብደብ የዘረፋ ሙከራ አደረጉ፡፡ የተቋሞቹ ተቀጣሪ ጥበቃዎች ግን ወደ ሰማይ ጥይት በመተኮስ ሌሎችም እንዲደርሱላቸው በማድረግ የዘራፊዎቹን ሴራ በትዕግስትና በብልሃት አመከኑ፡፡

በከተማዋ ያለው ሁኔታ ከሰላማው ጥያቄ ጀርባ ባሉ ፀረ ሰላም ሀይሎች አማካኝነት ወደ ስርዓት አልበኝነትና የገንዘብ ተቋማት ዘረፋ እየተሸጋገረ መሆኑን የተረዳው የክልሉ ልዩ ሃይል በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ወደ ከተማዋ ህግ ለማስከበር ገባ፡፡ እሱም ቢሆን ታዲያ ከሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰለባነት አልዳነም፡፡ <<ትራንስፎርመሩ በልዩ ሃይል ታጅቦ ሊሄድ ነው>> የሚል አሉባልታ በከተማዋ ተናፈሰ፡፡

የችግሩን መባባስ የተረዱ የዞኑ አመራሮች ከከተማዋ ህዝብ ጋር በትናንትናው እለት መክረዋል፡፡ በዚህ መድረክ የህዝቡ ጥያቄ በዋናነት ከመልማት ፍላጎት ጋር የተያያዘ ጥያቄ መሆኑ መግባባት ላይ ተደርሶበታል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ትራንስፎርመሩን ሳያውቁና ሳይመክሩበት ለመውሰድ መሞከሩ እንዳስቆጣቸው ገልፀው ጥያቄያቸው ሌሎች ፀረ ህዝብ ሃይሎች እንዳራገቡት ከልማት ውጭ አጀንዳ የሌለው መሆኑን፤ የልማት ፍላጎታቸው የሚሟላው ከመንግስት ጎን በመሆን በሚያደርጉት ርብርብ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በዚህም የህዝቡን ጥያቄ ለራሳቸው ድብቅ አላማ ማስፈፀሚያ ሊያደርጉ የነበሩ ሃይሎች ተጋልጠዋል፡፡

እንግዲህ እውነታው ይሄው ነው፡፡ መርሃቤቱ ከተማ ውስጥ ካሉ አጋሮቻቸው ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩ ፅንፈኛ ዲያስፓራ ተቃዋሚዎች ደግሞ ይህን በብዙ እጥፍ አባዝተው እየነገሩን ነው፡፡ በሀገር መበጣበጥ የሚደሰቱት እነ አቤ ቶክቻው ደግሞ <<መሬ ተነስቷል፤ ሌላው ይቀጥላል>> በሚል የፋሲል ደመወዝን “አለ ገና” ዘፈን ጋበዙን፡፡

እንዳማራችሁ ይቀራል፤ አሁን የአለምከተማ ህዝብ እንደተለመደው በፀረ ድህነት ትግሉ ላይ ተሰማርቷል፡፡ እናንተም ከሳምንት በላይ የሚቆይ አጀንዳ አላገኛችሁም፡፡ ግብዣችሁም ተቀባይ አላገኘም፡፡ በህዝቦች መካከል የጥላቻ መርዝ ለመርጨት የምታደርጉት ሙከራ ለዛሬ አልተሳካላችሁም፤ መቼም አይሳካላችሁም፡፡

እናንተ በፌስቡክ፤ በብሎግና በአፈቀላጤችሁ ኢሳት አማካኝነት የሌለ ጦርነት ከፍታችሁ በተኩስ ልውውጥ 11 ሰው እንደሞተና ሆስፒታሉ በቁስለኛ የወያኔ ወታደሮች መጨናነቁን ነገራችሁን፡፡ እውነታው ግን የተኩስ ልውውጥ የሚባል በቦታው ያልተከሰተ መሆኑ ነው፡፡ በርግጥ የጥበቃ ሃይሎች ድረሱልን በሚል ወደ ሰማይ ተኩሰዋል፡፡ ነገር ግን ከነሱ ጋር ተኩስ የገጠማቸው የለም፡፡ በጥቅሉ መሬ እናንተ እንደተመኛችሁት ጦሩን አልሰበቀም፡፡

ኢሳት በዘገባው አንድ የከተማዋ ነዋሪ ቆስሏል ብቻ ነው ያለው፡፡ አንድ ነዋሪ በማንና እንዴት እንደቆሰለ ባላረጋግጥም በለሊቱ ረብሻ ወቅት እንደቆሰለ እኔም ሰምቻለሁ፡፡ እንግዲህ ኢሳት እሱን ለማጣፈጫ ያክል ሊጠቀምበት ፈልጎ ይሆናል፡፡ ለማንኛውም ይሄ ነገር <<ለካ ኢሳትን ያለቅጥ ሲያስዋሸው የነበረው አንዳርጋቸው ፅጌ ነበር እንዴ?>> የሚል ጥያቄ ሽው እንዲልብኝ አድርጎኛል፡፡

ደግነቱ እዚህ አዲስ አበባ ያሉ ተቃዋሚዎች ይህን ዘገባ አልሰሙትም፤ ወይም ይችም ጭንቅላት የምትጠይቅ ሃሳብ ስለሆነች ወደ አዕምሯቸው አልመጣችላቸውም እንጂ <<እንጦጦ ማርያምን ልንሳለም ወጥተን ሳለ ድብልቅልቅ ያለ የተኩስ ድምፅ ከወደ መራቤቴ በኩል ሰምተናል>> ብለው ያደምቁት ነበር፡፡

ሰማያዊዎች፤ አታፍሩም እኮ እናንተ ደግሞ “ፍሪ ትራንስፎርመርና ወይንሸት ሞላ” ብላችሁ ቀውጡት አሉ፡፡ ዲያስፖራዎች ደግሞ በጀርመኗ በርሊን ከተማ “ትራንስፎርመር የማስለቀቅ ታላቅ ዘመቻ፤ በበርሊን” ብላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሩ አሉ፡፡ አለም ከተማ በቅርቡ ሂወታቸውን ባጡት ካርል ሄንዝ የተነሳ ከጀርመኖች ጋር ትስስር ስላላት ብዬ ነው የሰልፍ ቦታ የመረጥኩላችሁ፡፡

መረጃ የሰጣችሁኝን አመሰግናለሁ፡፡

—-

Kebede Kassa

more recommended stories