HRW፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይስ የኃያላን መንግሥታት መልዕክተኛ?

(ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል)

አሜሪካ ቅድመ ስኖውደን እና ድህረ ስኖውደን ያላትን ገጽታ አንድ አይደለም። ቅድመ ስኖውደን በነበረው ሁኔታ የተመለከትን እንደሆነ አሜሪካ የቻይና መንግሥት በአሜሪካ ቴክኖሎጂ የሳይበር ስለላ እንደሚያካሂድ በተደጋጋሚ በአደባባይ ስትከስ እንደነበርች የሚታወቅ ነው። ድህረ ስኖውደን ባለው ጊዜ ደግሞ አሜሪካ የቻይና መንግሥት መወንጀልዋ ቀርቶ የአሜሪካ የስለላ ጅርጅቶች የቻይና ትላልቅ ስኬታማ ኩባንያዎች ስትሰልል እንደነበረችና አየር ባየር መርጃዎችን ማሽሎክ የዕለተ ዕለት ሥራዋ እንደ ነበር በመረጃ የተደገፈ ምስክርነት ለማየት በቅተናል።

“ሁይማን ራይትስ ዎች” በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል HRW (1978) ተብሎ የሚታወቅ ድርጅት አብዛኞቹ በቀኝ ግዛት ስር ሲማቅቁ፤ ሀብት ንብረታቸው እየተዛቀና እየተመዘበረ ለረጅም ዘመናት የባርነት ጽዋ ሲጎነጩ የነበሩ የአፍሪካ አገራት ነጻ መውጣት ተከትሎ ሰብአዊ መብት በሚል ፈሊጥ በስልት ከተመሰረቱ ምዕራባውያን ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው።

የሰው ልጅ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚገረፍበት፣ የሚሰቃይበትና ከህያዋን በታች ከሙታን በታች ሆኖ እንደ ፋብሪካ ዕቃ ታሽጎ የሚቀመጥበት “ምድራዊ ሲዖል” ተብሎ የሚታወቀው “ጓተማላ” የሚሉት አሜሪካ ሰራሽ ገሃነም እያለ ቃሊቲን፤ ከቴክኖሎጂ ውጤት በተያያዘ ሆነ በምድሪትዋ በግልጽና በስውር የተተከሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ካሜራዎች የዜጎቹ የዕለተ ዕለት እንቅስቃሴ የሚሰልልና የሚከታተል እንዲሁም የዓለም ዜጎችና መንግስታት ውሎ ማደራቸውን የሚያነፈንፍ “ኤን.ኤስ.ኤ” እያለ በሁለት እግሩ ያልቆመ ቴሌኮም መክሰስና መወንጀል የሚቀናው HRW የሰብአዊ መብት ተሟጋች መሆኑን ቀርቶ ጸረ ሰብአዊ መብት መልዕክተኛ ድርጅት ሆኖ ሳገኘው ነገሩን አስደምሞኝ ይህችን አጭር ማስታወሻ አሰፍር ዘንድ ተገደድኩ።

ሁይማን ራይትስ ዎች “Ethiopia: Telecom Surveillance Chills Rights Foreign Technology Used to Spy on Opposition inside Country, Abroad” ሲል እ.አ.አ መጋቢት 25, 2014 ዓ.ም ከወደ በርሊን የለቀቀው መሰረተ ቢስ ክስና ተራ ውንጀላ “አሜን!” ብሎ የሚቀበል ዜጋ ቢኖር ዓይን እያለው የማያይ፣ ጆሮ እያለው የማይሰማ በአጭሩ እያለ የሌለ በቁሙ የሞተ (በድን) ዜጋ ብቻ ነው። በነገራችን ላይ “ኤን.ኤስ.ኤ” በተመለከተ CBS የቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ዋሽንግተን ፖስት’ እ.አ.አ መጋቢት 18, 2014 ለንባብ ያበቃውን ጽሑፍ ዋቢ አድርጎ የዘገበውን አጭር ትኩስ ዘገባ [http://www.youtube.com/watch?v=36W_MU_TjF4] ሊንክ በመጫን ይመልከቱ። (ሊያዩት የሚገባ) ሁይማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ሪፖርት ከዚህ አዲስ መገልጥ ኮርጆ ያቀረበው ሳይሆን አይቀርም።

ቀኑን በትክክል ባላስታውሰውም በኤድዋርድ ስኖውደን አማካኝነት ይፋ የሆነው “የኤን.ኤስ.ኤ” የስለላ ገበና ስያመቻምቹ የነበሩ የሰኔት አባላት ‘ሲ.አይ.ኤ’ እነሱን (የአሜሪካ የሰኔት አባላት ማለቴ ነው) ጭምር እንደሚሰልል ተደርሶበት ባለ ሥልጣኖቹ “HOW DARE YOU!” ሲሉ ምድር ቀውጠዋት ነበር። ታድያ HRW በሀገር ውስጥ (በአሜሪካ) የስለላ ሆነ ተያያዥ የሥራ ዘርፎች የማከናወን ምንም ዓይነት ሥልጣን የሌለው ‘ሲ.አይ.ኤ’ የአሜሪካ የሰኔት አባላት እንደሚሰልል በተጨማጭ ተረጋግጦ ጋማ መባሉ አላስነበበንም።

ህም! … የHRW ሹሞች ይህን ጥብስ የሆነ ዜና ሳይሰሙ ቀርተው ይሆን እንዴ? ወይስ ኒው ዮርክ የሚገኘው ዋና ቢሮ (የHRW) ከዋሽንግተን ይልቅ ለአዲስ አበባ ቅርብ መሆኑ ነው? ለመሆኑ HRW የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ የሚያነጣጥር ጠንካራ ትችት ሲያቀርብ ሆነ ሪፖርት ሲያደርግ ሰምተው ወይም አንብበው ያውቃሉ? ወጣም ወረደ በሰብአዊ መብት ስም፣ በፍትህ ስም፣ በነጻነት ስም … ወዘተ እየተባለ የአፍሪካ አገሮች መሪዎችና ህዝቦች ማሸማቀቅና ማሸበር ለምዕራባውያን ስትራቴጃዊ ነው።

ሕግ ለደካማ መንግሥታትና ለድሃ አገሮች እንጅ በኢኮኖሚና በወታደራዊ አቅማቸው ሚዛን ለሚደፉ በተለይ ለምዕራባውያን መንግስታት የማይሰራ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ህግ ብሎ ቋንቋ ከቀልድ ያለፈ የሚፈይደው የሌለው ትርጉም አልባ ለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው። አለ የሚባለው ህግ እንደሆነም እኛ ምስኪኖቹን እንጅ ምዕራባውያን አይመለከትም። እነሱ ራሳቸው ባወጡት ህግ የሚገዙ ምን በወጣቸው?

አንድ እውነት አለ ይኸውም፥ ምዕራባውያን የሚሰሩትና የሚያደርጉት ማንኛውም ሥራና ድርጊት ትክክል ሲሆን እነሱ የሚያደርጉትን ሌላ ሲያደርገው ግን ድርጊቱ ወንጀል መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከመኖር ወደ አለመኖር የሚያሻግር የአገር ማውደው፣ የመንግሥት መፍረስና የሕዝቦች መተረማመስ ሊያስከት የሚችል ከወንጀልም ወንጀል ሆኖ እናገኘዋልን።

የእንዲህ ዓይነት መሰረተ ቢስ ክስና ተራ ወንጀላ ዓላማ ምን እንደሆነ በምሳሌ ላስረዳ። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመት ቃለ ቀባይ ነበር ጀን ሳኪ ባሳለፍነው ሳምንት በክሪምያ የአልሞ ተኳሾቹ ምንነት በተመከተ ከመሬት ተነስተው “Stop the shooting in #Simferopol. Clear that #Russia shot first, and now must show restraint. #Ukraine @UkrProgress.” ሲሉ በትዊርተር ገጻቸው መጻፋቸው ይታወቃል። (ከመሬት ተነስተው ያለኩበት ምክንያት ትዊት ያደረጉት ጽሑፍ ማለትም ራሽያን ተጠያቂ ያደረጉበት ምክንያት ማስረጃ ያቀርቡ ዘንድ በውጭ ጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ነው።)

ታድያ ከላይ ወደ ታች በሚወርድ ቀጭኝ ትዕዛዝ መስመራቸው ጠብቀው ግዴታቸው የሚወጡ፤ ከዋኖቻቸው በቀመር ተሰልቶ የሚወረወር ቃል እንደ ተራበ አንበሳ ወሬ አሰፍስፈው የሚጠባበቁ 90 በመቶ የሚሆነው በስድስት ኮርፖሬት የሚዘወረው (ድጎማ የሚንቀሳቀሰው) የአሜሪካ ሚድያ የባለ ሥልጣንዋ ቃል ጭብጥ የሌለው ተራ ውንጀላ መሆኑ እያወቁ እሳቱን የማያያዝ የማንደድና የማራገብ ግዴታቸው በሚገባ ተወጥቷል። ሚድያዎቹ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር በሚያጎድፍ መልኩ ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ ቀን ተሌሊት የቀድሞ አፈ ቀላጤዋ ቃል ሲደጋግሙ ሚድያዎቹ ተዉ! የሚላቸው አካል አልነበረም። ምን ነው ቢሉ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ማሽን ናቸውና።

እንግዲያውስ፥ የሰማውን የማይጠይቅ የሚሰማውንና የሚያነበውን ሁሉ እውነት የሚመስለው ሰው ካለ የገዛ ራሱን ሰላም ለመንሳት የHRW ሪፖርት ሳይጠብቅ ጨርቁን ጥሎ ማበድ ይችላል። “HRW እንዲህ አለ” እያለሉ የክስ ዶሴ ለሚደረድሩ “The simpler the better” የሚሉት የጥፋት ፕሮፖጋንዳ መርህ ይህን ይመስላል ለማለት እወዳለሁ።

ጽሑፌን ሳጠቃልል የኃያላኖቹ ፖሊሲ አስፈጻሚ መልዕክተኞ ሆነው ሳሉ ዳሩ ግን “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” በሚል ሽፋን አቅመ ደካማ መንግሥታት ከህዝባቸው ጋር ሰላማዊ መቀባበል እንዳይኖራቸው አገራት እያመሱ የሚገኙ የሚገኙ ጸረ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ግብዝነት የምታጋልጥ ሁለት ደቂቃ የማትሞላ አስተማሪ ቪድዮ ጋብዤ ልለዮት።

[http://www.youtube.com/watch?v=NcAEjvT-Ri8] (ሊያዩት የሚገባ)

*Author can be reached at [email protected] & regularly writes at salsaywoyane.wordpress.com

*********

Guest Author

more recommended stories