የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ፓለቲከኞችና ፓለቲካቸዉ

(አቢይ ጨልቀባ ወርቁ)

መግቢያ፡- ይህ ፅሑፍ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ የኢህአዴግ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች እና ፖለቲከኞች በተለያዩ መድረኮች እና ፎሮሞች ስለ ራሳቸዉ እና አማራጭ የሚላቸዉ “ፓሊሲዎች” በሚናገሩበት፣በሚፅፍበት፤ ቃለ-መጠይቅ በሚሰጡበት ወቅት እየወሰደ፣ እያጣቀሰ ከፓለቲካዊ ፍልስፍና እንዲሁም ከነባራዊ የአገራችን ሁኔታ እየመዘዘ የአመክንዮ ሕፀፅ የሚያሳይ ነዉ፡፡ ለዚህ ፅሑፍ ሲባል ብቻ የኢህአዴግን የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ማለት በሰላማዊ መንገድ በአገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ከኢትዩጵያ ዉጭ ነፍጥ አንግበዉ የትጥቅ ትግል የጀመሩትን የሚያካትት ነዉ፡፡ ብእርና እስክርቢተዉ ይዘዉ በሚድያ በገዥዉ ፓለቲካ ፓርቲ ሰላማዊ እንዲሁም ሰለማዊ ያልሆነዉ ጦርነት የከፈቱት ያካትታል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ያደረጉት ዉይይት ምን ፍይዳ አለዉ?

የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች እና የአዉሮፓ ህብረት ፓርላማ የሰብአዊ መብት ንኡስ ኮሚቴ ተወካዮች ስለ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ሐምሌ 9፣ 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዉይይት አካሂደዉ ነበር፡፡ በዉይይት መድረኩ ላይ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፣ዶ/ር መረራን ጉዲና እና አቶ ጥላሁን እንደሻዉ የተገኙ ሲሆን አቶ አበባዉ መሓሪ ደግሞ ከመኢኣድ ተገኝተዉ ነበር፡፡ የሰማያዊ ፓለቲካ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ስብሰባዉ ላይ ተገኝተዉ ነበር፡፡ ከተነሱት ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል የፓለቲካ ምህዳር መጥበቡ፣የፀረ-ሽብር ሕጉ ጋዜጠኞች እና ፓለቲከኞች ራሳቸዉ ሳንሱር እንዲያደርጉ የእጃ ዙር ጭንቀት እየጣላቸዉ መሆኑ ለህብረቱ ሉኡካን ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት እንዲሁም የፕሬስ ሕጎች ላይ ያላቸዉ ተቃዉሞ አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ከአሁን በፊት ቡዙ ጊዜ የተነሱ እና ክርክር የተደረገባቸዉ ሲሆኑ ለዚህ ፅሑፍ ሲባል ጉዳዩን ለጊዜዉ እተወዋለሁ፡፡

ለአሁኑ ግን የሕብረት አባለቱ ተወካዮች ከተቃዋሚ ፓለቲከኞች የተናገሩት አንድ እና ሁለት ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

አንደኛዉ “ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች አገሮች ችግር ላይ ወድቃ፣ የአለም አቀፍ አስከባሪ ሃይል ከመመደብ በፊት የሕብረቱ አባላት ወዳጃቸዉ የሆነዉ ኢህአዴግ መምከር እንዳለባቸዉ”፣ ለሕብረቱ ተወካዮች ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛዉ “ኢህአዴግ በአመት 3.9 ቢልዮን ዶላር እርዳታ እያገኘ ቢሆንም፣ የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ስልጣን ቢይዙ አሁን ኢህአዴግ እያስመዘገበ ካለዉ የኢኮኖሚ እድገት በላይ ማስመዝገብ እንደሚችሉ”፣ ለሕብረቱ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ንግግሮች አንድ በአንድ ከመፈተሻችን በፊት፣ ስለ ታላቁ የ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ድንቅ የአሜሪካዉ ፓለቲከኛ ቲፕ ኦኔል ትንሽ ላዉራቹ፡፡ ምክንያቱም ከላይ የተጠቀሱት ንግግሮች የሚያስረዳ እና ለነገረ-ጉዳዩ ለማስረዳት ወሳኝ ስለ ሆነ ነዉ፡፡

ቲፕ ኦኔል ሁሉም ፓለቲካ አካባቢያዊ ናቸዉ (All Politics is local) ብለዉ በሰየሙት መፅሓፉቸዉ እንደሚከተለዉ ብለዋል፡፡ “term limits are baloney. Stick with the old oaks in a storm (የስልጣን ጊዜ ገደብ ትርጉም የላቸዉም፡፡ ማእበል በመጣ ወቅት ያረጀዉ ዛፍ ግጥም አድርገህ ያዝ)” በሚለዉ ክፍል ላይ፡-

“you need to have the men and woman with experience when the nation needs courage and stability. Put in terms limits and you rob the nation of its best people in a time of need. …Do not put an artificial limit on quality. That is a big mistake (አገሪታን መረጋጋት እና ብርታት ባስፈለጋት ወቅት፣ ልምድ ያላቸዉ ወንዶች እና ሴቶች ያስፈልጋሉ፡፡የስልጣን ጊዜ ገደብ ፣ ገደብ ይደረግበት፡፡ ከዛ አገሪታን አለኝ የምትላቸዉ ሰዎች እዉቀት መጠቀም ነዉ፡፡ጥራት ላይ አላስፈላጊ ገደብ አለ ማስቀመጥ፡፡ ያንን ማድረግ ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡ )”

ብለዉ በገፅ 141 እና 142 አስፍረዋል፡፡

ይህ ለማለት ያስደፈራቸዉ በሃምሳ አመት በላይ የፓለቲካ ሂወት ቆይታቸዉ ላይ ያዩት እና የተገነዘቡት ጉዳይ ነዉ፡፡ ለምሳሌ የ1930 ዎች የአሜሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ዝቅተት(Americas Great Depression) እንዲሁም ሁለተኛ የአለም ጦርነት አሜሪካ ልምድ ያለዉ እና በሳል መሪ ባታገኝ ኑሮ የአሁና ታላቅ እና ልእለ ሃያላን አሜሪካን ባላየን ነበር፡፡ ስለሆነም የቲፕ ኦኔል ትልቁ ምክር ፣ የፓለቲካ ልምድ ወሳኛ መሆኑ ነዉ፡፡ በኢትዩጵያም ይህን እዉነታ የሚቀየር አይሆንም፡፡ ሊቀየርም አይችልም፡፡

የቲፕ ኦኔል እይታ (analytical framework) በመነሳት የኢንጅነር ይልቃል እንዲሁም የሌሎች ፓለቲከኞች በህብረቱ ልኡካን ፊት የተናገሩት መመርመር ይቻላል፣ ከልምድ ያላቸዉ ፓለቲከኞች ከሚናገሩት አካያ ማለት ነዉ፡፡

የመጀመርያዉ ንግግር “ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች አገሮች ችግር ላይ ወድቃ የአለም አቀፍ አስከባሪ ሃይል ከመመደቡ በፊት..” የሚለዉ የበሰለ ፓለቲከኛ የሚናገረዉ እንዳይደለ የሕብረቱ ተወካዮች በሰከንዶች ዉስጥ የሚረዱት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ለመሆኑ እዉነት ኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ የሚያስፈልጋት አገር ናት? የሕብረቱ ተወካዮች ኢንጅነር ይልቃል የተናገሩት የተለየ አቋም እንደሚኞራቸዉ ግልፅ ነዉ፡፡ ስለ ሰላም እና ደህንነት ጠለቅ ያለ እዉቀት የሌለዉ ከኢንጅነር ይልቃል የተለየ አቋም እንደሚኖረዉ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነዉ፡፡

እዚህ መጨመር ምፈልገዉ ነገር ቢኖር አሁንም ቲፕ ኦኔል ሁሉም ፓለቲካ አካባቢያዊ ናቸዉ(All Politics is local) ባለዉ በድጋሚ በገፅ 59 ስለ ቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ነበር፣ ስለ ጃክ ኬኔዲ አንድ ታሪክ ይነግሩናል፡፡ በአንድ ወቅት ጃክ ኬኔዲ በምርጫ ምረጡኛ ቅስቀሳ ላይ ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በስራ በጣም ተወጥረዉ ስለ ነበር፤የጊዜ እጥረት ነበረባቸዉ፡፡ አንድ ቀን በቦስተን የሚገኝዉ የአዲሱ ኢንግላንድ መጣቶች የካቶሊክ ድርጅት አባላት ለማግኝት ይወስናሉ፡፡ ከድርጅቱ ሊቀ መንበርም ቀጠሮ ይዘዉ፣ ወጣቶችን ለማግኝት ቀን ቀጠሮ ይቆርጣሉ፡፡ ሆኖም በተባለዉ ቀን በድርጅቱ ከሚገባ በላይ ሰዉ ነበር፡፡ የጃክ ኬኔዲ ጊዜ ላይ ጫና ስለ ሚያሳድር ሁለት ቡዱን ላይ ይከፈላሉ፡፡ አማራጭ ይቀርብላቸዉ እና ማንን ለማግኝት እንደወሰኑ ጥያቄ ይቀርብላቸዋል፡፡ አንደኛዉ የወጣት መኖክሴ ስብስብ ሲሆኑ በቁጥር በዛ ያሉ ነበሩ፡፡ ሁለተኛዉ የጰጳሳት ስብስብ ሲሆን ጥቂት ቁጥር ያላቸዉ ግን ታዋቂ ሰዎች ያካተተ ነበር፡፡ ስለ ሆነም ጃክ ኬኔዲ በጊዜ እጥረት ምክንያት አንዳቸዉ ብቻ ማየት ነበረባቸዉ፡፡ በዚህ ወቅት ጃክ ኬኔዲ ያለ ምንም ማመንታት ወጣት ሴት መነኩሴዎቹን ለማየት ይወስናሉ፡፡ እንደሚከተለዉም ብለዉ ነበር፤” The nuns I will see. But not the bishops. They all vote Republican. (ሴት መኖክሴዎቹ ለማየት እፈልሃለሁ፡፡ ጳጳሳቶቹነ ግን ሁሌ ለሪፓብሊካን ስለ ሚመርጡ ትቻቸዋለሁ” ብለዉ ነበር፡፡

ይህ ወደ እኛ አገር ፓለቲካ ሲተረገም ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲ ከአሁን በፊት በ1997 ዓ.ም ወቅት ድጋፍ ያገኙባቸዉ ቦታዎች ስንመለከት በአዲስ አበባና እንዲሁም በተወሰኑ የክልል ከተሞች የታጠረ ነበር፡፡ ግን የ2002 ዓ.ም ምርጫ ዉጤት የ1997 ዓ.ም ድጋፋቸዉ በዚሮ ያባዘዉ ነበር፡፡ ይህ አንድ አና አነድ ነገር ብቻ ያሳያል፡፡እሱም የኢትዮጵያ ሰፊ የሆነዉ ገበሬ በጎናቸዉ ማሰለፍ እስካል ቻሉ ድረስ አራት ኪሎ ገብቼ አገር አስተዳድራለሁ ማለት ዘበት ነዉ፡፡

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አፈትልኮ የወጣዉ ድምፅ የፀረ ሽብር ሕጉ አሁንም አስፈላጊ መሆኑ አንድ ማስረጃ ነዉ!

የ‹ግንቦት 7› ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከባዕዳን ስለተቀበሉን ገንዘብ፣ የኢሳት ድርሻ እና ተያያዥ ጉዳዮች ለድርጅታቸዉ አመራሮች ገለፃ የሰጡት ሚስጥራዊ ስብሰባዎች ሁለት ቅጂ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አፈትልኮ ወጥቶ መሰራጨቱ ይታወሳል፡፡ ከዚ በታች የምዘረዝረዉ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሚስጥራዊ ንግግር የፀረ ሽብር ሕጉ አሁንም አስፈላጊ መሆኑ አንድ ማስረጃ ነዉ፡፡ ስለሆነም የመጀመርያዉ የድምፅ ቅጂ ላይ ያለዉ የብርሃኑን ንግግር በፅሑፍ በመገልበጥ እንደሚከተለዉ አቀርበዋለሁ፡፡

“ አራት ሆነን ሄደናል፡፡ አንድ ሙሉ ቀን የፈጀ ዉይይት አድርገናል፡፡ ዋናዉ ሰዉየ አልመጡም: ከሳቸዉ ቀጥሎ ያለው ሰዉ ነዉ [የመጣው] እና ባለፈዉ ጊዜ የወጣዉ ዝርዝር አጀንዳ ላይ ከሞላ ጎደል በሁሉም ላይ ነዉ የሄድንባቸዉ፡፡

ከዚህ በፊት በነበረን ስምምነት እና ባቀረብነዉ በጀት መሠረት ስድስተኛዉ ወሩ ስለደረሰ፣ የሚቀጥለዉን tranche (ዙር  ክፍያ) አንድ አምስት መቶ ሺ ነበር፡፡ እሱ እንዲሰጠን ጠይቀን በሱ ላይ ስምምነት ተደርሳል፡፡

ከዛ ዉስጥ ሁለት መቶ [ሺህ] በደህንትት እና መከላከያ ለሚሠራዉ ሥራ ነዉ፡፡ እሱ እዛዉ በዱባይ በኩል የሚሰጥ ነዉ፡፡

ሌላዉ ሁለት መቶ [ሺህ] ለኢሳት(ESAT) ሥራዎች የሚዉል ነዉ፡፡

አንድ መቶ [ሺህ] ግን በሀገር ዉስጥ በሰላማዊ መንገድ ለሚሰራዉ እና ለዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በሚል ነዉ የቀረበዉ በጀት፡፡ በዛ መሰረት አምስት መቶ [ሺህ] ተፈቅዷል፡፡

You know, “thank you ምናምን” ሲሏቸዉ ነበር ለዚህ ለሰጡት  እነ ዳዊት፤  ”no no ይህ thank you የሚያስፈልገዉ አይደለም ይህ ለራሳችን ብለን ነዉ የምንሰራዉ” [አሉን]፡፡

ከዛ ሶስት መቶ [ሺህ] ዉስጥ 150 [ሺህ] እዛዉ እናንተ ጋር ለንደን እና ሌላ 150 [ሺህ] እዚህ እንዲሰጥ ነዉ የተስማማነዉ፡፡ That should be available soon.

Everything went very smoothly and very very positive.

በዲፕሎማሲውም በኩል ስለለምንሰራቸዉ ስራዎች በተወሰነ ደረጃ ተነጋግረናል፡፡ በአዉሮፓ እ በአሜሪካ በተወሰነ ደረጃ coordinate ለማድረግ፡፡

በተለይም ደግሞ directly(በቀጥታ) በስቴት ዲፓርትመንት (በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር) በኩል ልናረግ የምንችለዉ ነገር የለም፡፡ but we are working በኮንግረስ (የአሜሪካ ፓርላማ) በኩል እና በአንዳንድ በቲንክ ታንኮች ግሩፕ በኩል ሰዎችን attract ለማድረግ concerted effort (የተቀናጀ ጥረት) ጀምረናል፡፡

እንግዲህ ያ ዉጤት ያመጣል ብለን የምናስበዉ፤ if there is a significant voice against የኢትዮጵያ መንግስት በኮንግረስ ውስጥ እና በቲንክ ታንኮቹ ውስጥ [ከተፈጠረ]….እንደዛ እንደዛ ዓይነት doubt እና serious questions (ጥርጣሬና ጥያቄ) [ከተፈጠረ ነው]፡፡

so towards that end…….ኮንግረሱ በሚመለከት ኖቶቻችን compare እያደረግን እና እነኚህ ቲንክ ታንኮችን ምናምኖችን approach እያደረግን effectively ከሰራን through time እንትን ማግኘት እንችላለን፡፡ at least sufficient questions እና doubts እንዲቀመጥ ማድረግ እንችላለን፡፡

በሌላ front የጀመርነዉ ስራ ነበር ከነሱ የማስታወቅያ ሰዉ ጋር፡፡ ከዚህ በፊት ሪፖርት አድርጌላችሁ ነበር አንድ ትራንስፎርመር  ከነሙሉዉ እንትኑ build ማድረግ፡፡ እና አቅጣጫዉ completely  ኢትዮጵያ ላይ focus እንዲያደርግ አድርጎ powerful የሆነ እንትን dedicate ሁኖ መስራት ይቻላል የሚለዉ:: መጀመርያ አዲስ ለመፈለግ ዉድ ሁኖ ነበር፣ አሁን ተገኝታል::

ወደዛ ለመሄድ የተዘጋጁ 7 ሰዎች ከደቡብ አፍሪካ ነበሩ፡፡ by yesterday it was finished የነሱ፡፡ ሌላ ሶስት ሰዎች አሉ፡፡ ሁለት ከደቡብ ሱዳን እና አንድ ከኬንያ የሚሄዱ፡፡ የነሱ ነገር ዛሬ ተነጋግረን ጨርሰናል፡፡ የነሱም ነገር ያልቃል፡፡ so እነሱ በሙሉ ሲገቡ አንድ ሙሉ ጋንታ የሚሆን የመጀመርያዉ ዙር እንትን ማድረግ የሚችል አባል ይኖራል፡፡

እሱን ቶሎ ብሎ ማስጀመር ከዛ በኋላ ከዉስጥ የሚወጡትን ሰዎችን ጨምሮ ወደ ፊት የመሄድ ስራ ነዉ፡፡

so በነሱ በኩል whatever necessary ይህን strong የሆነ foundation ያለዉ የኛ ነገር መመስረቱ ላይ ስምምነት አለ፡፡

ይሄ እዛ ዉስጥ ያሉት የማሰባሰብ ነገር ብታምኑም ባታምኑም የግንቦት ሰባት ህዝባዊ የሚለዉ ስም አንቀበልም ብለዉ እኛ ከዉይይቱ ወጥተናል፡፡ ይህን ነገር አንቀበልም የሚሉት እንደተጠበቀዉ የአርበኞች ግንባር እና ይህ የአማራዉ ድርጅት የሚባለዉ ነዉ፡፡ ግን እዛ ያለዉ ይህን handle የሚያደርገዉ የኤርትራ እንትን ግንቦት ሰባት እዚህ agreement ውስጥ ስለሌለ እዛ መግባት እንፈልጋለን የሚሉ አዉነተኛ እና ትክክል እስከ ሆነ ድረስ የመግባት መብታቸዉ የተጠበቀ ነዉ ብለዋል፡፡so ከዛ በኩል አንድ ሌላ issue ተፈጥረዋል”፡፡

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ንግግር በደንብ ያጤነ ሁለት ነገሮች መገንዘብ ይችላል፡፡

አንደኛዉ በኢትዮጵያ “በሰላማዊ መንገድ” የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች እንዲሁም ጋዜጠኞች በኤርትራ በኩል በጀት እንደሚመደብላቸዉ ነዉ፡፡ በጋዜጠኛነት ስም ጋዜጣ እያቋቋሙ ሽብርን የሚቀሰቅሱ የስራ ማስኬጃ ብር ከኤርትራ መንግስት እንደሚመደብላቸዉ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለዉም፡፡ ምክንያቱም “አንድ መቶ [ሺህ] በሀገር ዉስጥ በሰላማዊ መንገድ ለሚሰራዉ እና ለዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በሚል ነዉ የቀረበዉ በጀት” የምትለዉ ንግግር የሚያሳየዉ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚቀበል ፓለቲከኛ ወይም ጋዜጠኛ አለ ማለት ነዉ፡ ያዉም በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚል ሃይል፡፡ ይህ ዉንጀላ ግን ለሁሉም የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ይሰራል ማለት ግን አይደለም፡፡

ሁለተኛዉ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኤርትራ መንግሰት ፌት አዉራሪነት በግንቦት 7 ተላላኪነት በኢሳት በኩል የፕሮፓጋንዳ ጦርነት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እንደከፈተ የሚያሳይ ነዉ፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ የኤርትራን መንግስት ግዳጅ ተቀብሎ ኢትዮጵያን የማተራመስ እስትራተጂ እያስፈፀመ ነዉ ማለት ነዉ፡፡

ይህን ማሳያ የሆኑ ሁለት ክስተቶች በቅርብ ተከስተዋል፡፡

አንደኛዉ ፓሊሲ አማጪ(think thank) አንድ የመታገያ መሳርያ በማድረግ ግንቦት 7 እና የኤርትራ መንግስት እጅ እና ጋንት ሁነዉ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ራሱ ነፃ የፓሊሲ አማጪ አድርጎ የሚቆጥር ግን በተጨባጭ በኤርትራ በኩል በጀት ተሰሉተለት የሚያስተነፍሰዉ የኦክላንድ የምርምር ተቋም (Oakland institute) ኢትዮጵያን የማተራመስ እስትራተጂ አንድ አካል ነዉ፡፡ በቅርብ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ሁለት ተከታታይ ጥናት አቅሩባል፡፡ የጥናቶቹ ይዘት ለመረዳት እንደሚቻለዉ የኢትዮጵያ መንግስት የሚቀበለዉ የልማት እርዳታ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ እርዳታዉ ላይ ጥላ እሸት ለመቀባት እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት የማዳከም እስትራተጂ አካል ነዉ፡፡ ይሳካል ወይስ አይሳካም የሚለዉ ቀጣይ የምናየዉ ቢሆንም የግንቦት ሰባት የኤርትራ ተላላኪነት በመረጃ ብቻ ሳይሆን በማስረጃም ጭምር ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ ነዉ፡፡

ሁለተኛዉ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ኮንግረስ በኩል የሚያደርጉት ጥረት ነዉ፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ለአሜሪካ ኮንግረስ በቅርቡ የሚከተለዉ ብለዉ ነዉ፡፡ “የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ፡፡ ይህ አባባል አቶ ይልቃል የአዉሮፓ ሕብረት የሰብአዊ መብቶች ንኡስ ኮሚቴ ፊት ላይ የተናገሩት በይዘት ተመሳሳይ ነዉ፡፡ አሁን ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ የእርስ በእርስ ጦርነት ኢትዮጵያ ላይ ይኖራል ብሉ መተንተን ይቅርና ፣ ማሰብ ለራሱ አስቸጋሪ ቢሆንም የሁሉቱም ንግግሮች ገጠመኛ ብቻ ነዉ ብሎ ማለፍ ግን ይከብዳል፡፡ ስለሆነም በኤርትራ መንግስት አቀባይነት፣ እንዲሁም በግንቦት 7 ተላላኪነት በሆኑበት ሁኔታ አሁንም የፀረ-ሽብሩ ሕግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሁለተኛዉ አፈትልኮ የወጣዉ ንግግር እንድምታ

የሁለተኛዉን የድምፅ ቅጂ ላይ ያለዉ የዶ/ር ብርሃኑ ንግግር በፅሑፍ በመገልበጥ እንደሚከተለዉ አቀርበዋለሁ፡፡ ከዛ ብሃላ ያለዉ እንድምታ ለማስረዳት እሞክራለሁ፡፡

“በነሱ በኩል ያለዉ view (አመለካከት) እንደገለፅሉን the remaining each and every political (የተቀሩት እያንዳንዳቸዉ የፓለቲካ) ድርጅት እዛ የሚንቀሳቀሱ strength and weakness assesement (ጠንካራ እና ደካማ ጎናቸዉ በመፈተሽ) ጋር ተነጋግረን እና we arrived at series of conclusion (ተከታታይ የሆኑ ድምዳሜዎች ደርሰናል). And based on those conclustions (በድምዳሜዉ መሰረት) እንዴት ወደ ፊት እንደምንሄድ directions (አቅጣጫዎች) አስቀምጠን ነዉ የተለያየ ነዉ፡፡”

“በግንቦት 7 በተመለከተ የሚያደረገዉ እንቅስቃሴ በሚመለከት እንደ በፊቱ የሚደረገዉ ዝም ብሎ all type of small groups (ሁሉም አይነት ትናንሽ ቡዱኖች) እንትና እያደረጉ መቀጠል ምንም ዉጤት የማያመጣ መሆኑ ስምምነት አለ፡፡ እያንዳንዳቸዉ በዝርዝር ከተመለከትን ብሃላ based on our assesement(በግምገማዉ መሰረት) እና የነሱ assesement(ግምገማ) both (ሁለቱም) ኦብነግ እና ኦነግ ለጊዜዉ ተዋቸዉ፡፡”

“በዚህ በኩል ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ በደንብ ስንጀመር then (ከዛ) ዉይይት ማድረግ ይቻላል፡፡ so far as እነሱን concerned the only two group that matters (ሁለት ትርጉም ያላቸዉ ቡዱኖች በተመለከተ) ይህን effectively (የተሳካ) ለማድረግ ሁለት ናቸዉ ብሎ ያምናል፡፡ ይህም ደምሒትና እኛን ነዉ የሚያምኑት፡፡ ደምሒት strength(ጥንካሬዉ) አለዉ፡፡ ወታደራዊ strength (ጥንካሬዉ) አለዉ፡፡ እናንተም ፓለቲካዊ strength (ጥንካሬዉ) አለቹ፡፡ እናንተ የራሳቹ capacity(አቅም) በተሎ ብሎ bulid(መገንባት) ማድረግ ነዉ፡፡ ግን በናንተና በደምሒት በኩል ስምምነት ከተደረሰና እና መግባባት ካለ ሌሊቹ will fall into line (ወደ መስመሩ ይገባሉ). They are not that important (ያን ያክል ጠቃሚ አይደሉም) የሚል ነዉ፡፡ so donot even think about them (ስለ እነሱ ጭራሽ አታስቡ). Speciciaclly (በተለይም ደግሞ) ስለ አርበኞች ግንባር፡፡ የትም የሚሄዱ አይደሉም እነሱ፡፡ ግን ሌሎች የጋምቤላ፣የቤንሻንጉል እና የሚባሉት they will eventually come (በስተመጨረሻ ይመጣሉ) because (ምክንያቱም) ያለ ደምሒት ምንም capacity (አቅም) ያላቸዉ አይደሉም፡፡”

“ So lets concentrate on ( ትኩረታችን እዚ ላይ እናድርግ)፡፡ አምደኛዉ የcapacity follow (የአቅም ግንባታ ክትትል) የሚደረግበት ሲሆን ሁለተኛዉ እናንተና ደምሒት በጋራ ሁናቹ መንቀሳቀስ የምንችል እና እነዚህ ሁኔታ build (ግንባታ) ማድረግ so this be the priority(ይህ ቅድሚያ የሚሰጠዉ) የሚለዉ ተስማምተናል፡፡ በአንፃሩም እኛ እየሄድንበት ያለዉ አካሄድ አስረድተናል፡፡ and there is full agreement (ሙሉ ስምምነት አለ) እና ይህን ለማድረግ በምናደርገዉ እንቅስቃሴ ቶሎ ብሎ quake (ፈጣን) የሆነ response (መልስ) እንዲሰጠን እና ትብብር እንዲደረግልን በዛ በኩል ምንም ጥያቄ የለዉም፡፡ we will give you what ever is necessary (አስፈላጊዉ የሆነዉ ማንኛዉ ነገር እንሰጣቹሃለን) እና within our capacity(አቅማችን የፈቀደዉ ሁሉ)፡፡”

“አዲሱ ሁኔታ ይህ የአማራ ድርጅት ተብሎ የተቋቋመዉ ዉስጥ ያሉት ወደ 21 የሚሆኑ የነሱ ተጋዳዮች ተሰብስበዉ ተፈራርመዉ እናም ከፊት ግንቦት 7 ብለን የመጣነዉ there fore (ስለሆነም) አማራ ዉስጥ ያሉት አመራሮች ለመመራት እና እና ወደ ፊት መሄድ አንችልም፡፡ ወደ ግንቦት 7 እንትን ለማድረግ ፍቀዱልን የሚል ጥያቄዎች ወደ ኤርትራኖች እዛ ምድር ላሉት የነሱ እንትናን ጠይቀዋል፡፡ so እነሱ ተገደዉ accept (የሚቀበሉት) ድርጅቱን የማይመሩ፡፡ ይህ ድርጅት as (እንደ) ድርጅት function (ሰርቶ) አድርጎ አንድ ነገር ያመጣል የሚል ነገር የለዉም፡፡ this (ይህ) ለኛ ብቻ አይደለም ለኤርትራኖች it is true (እዉነት ነዉ)፡፡They are just there ( ዝምብለዉ ነዉ እዛዉ ያሉት)፡፡ ለሱሙ ብቻ they are there (እዛ ያሉት)፡፡”

“ከነሱ ላይ አንድ እና ሁለት የምንባባለዉ ነገር የለም፡፡ እዚህ ዉስጥ ገብተዉ ለመስራት ፍቃደኘነት እንትን ካለ ግን resist (ተቃዉሞ) የሚያደርጉት እነሱ ናቸዉ፡፡ እነሱ ናቸዉ problem (ችግር) እየፈጠሩ ያሉት፡፡ any time (በማንኛዉ ሰአት) እንደዚህ ተባብሮ የመስራት ነገር ሲመጣ ሁሉ ጊዜ ልንዋጥ፣እንትል ልንሆን ነዉ በሚል ፍራቻ እንትን እያደረጉት ያሉት እነሱ ናቸዉ፡፡ So let them do what ever they do and lets us do what ever we do( የሚያደርጉት ነገር ያድርጉ፣እኛም የምናደርገዉ ነገር እናድርግ)፡፡ እነሱ እንደዚህ ናቸዉ ፣አይረብም የሚል ነገር ዉስጥ አንገባም፡፡ But our media(ግን የኛ ሚድያ) ከአሁን ቡሃላ including (እንትናን ጨምሮ) ኢሳት የሌላቸዉ ነገር እያወጣ የሚናገረዉ ነገር ያቆማል፡፡ ከዛ በተግባር የሚያሳዩት እና እንትን የሚሉት ካለ ያድርጉ፡፡ አለበለዝያ ሰዉ ሁሉ መሆን ከፈለገ lets them continue do (ይቀጥሉ የሚያድርጉት). What are we going to do? ( ምን ማድረግ እንችላለን?)፡፡”

አፈትልኮ የወጣዉ ሁለተኛዉ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ድምፅ ቅጂ በዋናነት የሚያመላክተዉ የኤርትራ መንግስት የኢትዩጵያን መንግስት የሚፋለሙ ነፍጥ ያነገቡ ታጣቂ ሃይሎች ምንም ጉልበት እንደሌላቸዉ ነዉ፡፡

የንግግሩ መንፈስ እና መልእክት ሁለት ነገሮች ያሳያሉ፡፡

አንደኛዉ ዶ/ር ብርሃኑ በግልፅ ከኤርትራ መንግስት እርዳታ እንደሚደረግላቸዉ በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡ አሁን መታየት ያለበት የኤርትራ መንግስት ለግንቦት 7 የፈለገዉ ድጋፍ ቢያደርግ ትርጉም የለዉም፡፡ ግንቦት 7 ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ከፈለገ መጀመርያ በኢትዩጵያ ህዝብ ፊት ተቀባይነት ማግኝት አለበት፡፡ ይቅርና ግንቦት 7፤ የኤርትራ መንግሰት ራሱ በብዙ መንግስታት ተደግፎ ኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት መገልበጥ ወይም ማስገልበጥ ተስኖታል፡፡

ሁለተኛዉ የተለያዩ ነፍጥ ያነገቡ የኢትዩጵያን መንግስት የሚፋለሙ ምንም ጉልበት እንደሌላቸዉ እንዲሁም የኤርትራ መንግሰት ራሱ ተስፋ እንደቆረጠ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምስክርነታቸዉ ገልፀዋል፡፡ ኦነግ እና ኦብነግ ያበቃላቸዉ ትርጉም እንደሌላቸዉ የኤርትራ መንግስት ግምገማ ያሳያል፡፡ አርበኞች ግንባር ብሎ ራሱ የሚጠራ ትርጉም የሌለዉ ሃይል እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደገና ምስክርነታቸዉ ገልፀዋል፡፡ በግንቦት 7 እና አርበኞች ግንባር አለመጣጣም እንዳለ እንዲሁም አርበኞች ግንባር ከግንቦት 7 ጋር ካልተስማማ የኢሳት እና ሌሎች ሚድያ ሽፍን ማግኘት እንደማይችል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አስጠንቅቀዋል፡፡ በኤርትራ መንግስት ተስፋ የተጣለበት ደምሒት ተብሎ የሚጠራ ሌላ ታጣቂ ሃይል ነዉ፡፡ የትግራይ ህዝብ ሆድ ያልወጣ የትግራይ ህዝብ የማይደግፈዉ ደምሒት ላይ ተስፋ ማድረግ በሰማይ ላም አለኛ ነዉ ነገሩ፡፡

የአልጀዚራ ፕሮግራም እና የኦነግ የሙት መንፈስ!

ራሱ “የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር” ብሎ የሚጠራ ቡዱን አባላት ከአልጀዚራ ስትሪም ፕሮግራም ስለ ኦሮሞ ህዝብ በተመለከተ ለማዉራት ቀርበዉ ነበር፡፡ ከቀረቡት እንግዶች መሃል አቶ ጀዋር መሓመድ (የኦሮሞ መብት ተማጋች ባይ/ በነገራችን ላይ የኦነግ አባል አይደለሁም ይላሉ) ፣ አቶ መሓመድ ኤደሞ (የ O pride ድህረ ገፅ ባለቤት) እንዲሁም ፊዶ ኢባ(የኦነግ ዉጭ ጉዳይ ሃላፊ) ነበሩ፡፡ በዉይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርታል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ኦነግ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀ ስለሆነ ማንም የመንግስት ተወካይ ከኦነግ ጋር በጠረቤዛ ወይም የሚድያ ክርክር ላለ ማድረግ ስለ ወሰነ ነዉ፡፡ ይህ እንደ ተጠበቀ ሁኖ ኦነግ የሚባል ድርጅት አለ ብየ በግሌ አላምንም፣ ኦነግ የሚባል የሞተ መንፈስ ግን እንዳለ ይሰማኛል፡፡ የኦነግ ሞት እንደገና ሂወት ለመስጠት የሚደረግ ሙከራ የፈለገዉ ግዜ ይዉሰድ ፤ እዉነት ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡ ኦነግ የሚባል የሙታን መንፈስ ከመወለዱ በፊት ነዉ የሞተዉ፡፡ አንድ ሺ የአለም አቀፍ ሽፋን ቢያገኛም እንደገና ሂወት ሊኖረዉ አይችልም፡፡ በሚከተለዉ አንድ አብይ ምክንያት፡፡

እንደሚታወቀዉ አንድ ቡዱን ወይም ታጣቂ ሃይል የፈለገዉ አላማ ይኑረዉ፣ ተጨባጭ የአገሪታን ነባራዊ ሁኔታ እና ትክክለኛ ታሪክ ያገናዘበ አቃም መዉሰድ አለበት፡፡ ለምሳሌ ህ.ወ.ሓ.ት የትጥቅ ትግሉ ስትጀምር የመገንጠል ጥያቄ ይዛ ነበር የተነሳችዉ፡፡ “ታላቋ ትግራይ” የመፍጠር ቅዥት ልበለዉ፡፡ ሆኖም የትጥቅ ትግሉ የስድስት ወር እድሜ እንዳስቆጠረ ህ.ወ.ሓ.ት እርምት ወሰደ፡፡ ትግራይ ከኢትዩጵያ መገንጠል አላማ፣ ታሪክ በምንም መልኩ እንደማይደግፋት አወቀች፡፡ የትግራይ ህዝብም ቢሆን ለህ.ወ.ሓ.ት ታጋዮች እዉነታዉ የነገራቸዉ በስድስተኛዉ ወር ላይ ነበር፡፡ ስለሆነም የህ.ወ.ሓ.ት ብልጣ ብልጥነት እዚህ ጋር ነዉ፡፡ ህ.ወ.ሓ.ት ስህተቱን አምኖ በጊዜዉ በወሰደዉ እርምት ምክንያት ከሌሎች አጋር ድርጅቶች በመተባበር ደርግን ለመጣል በቃ፡፡

የኦነግ የፓለቲካ ፕሮግራም ግን በበቂ ሁኔታ በታሪክ የሚደገፍ አይደለም፡፡ ኦነግ ህ.ወ.ሓ.ትን በስድስተኛዉ ወር ያረመዉ ስህተት የኣርባ አመት ጎልማሳ ሁኖም ከስህተቱ ለመማር አልፈለገም፡፡ የኦነግ የኢትዩጵያ የመቶ አመት ታሪክ እና የአቢሲንያ ወረራ የጥቂት የኦነግ የታሪክ ሙሁራን ዉጤት ነዉ፡፡ በተለይም የኦሮሞ ሊሂቃን ህዝብ የወራሪም እንዲሁም የተወራሪ ታሪክ ነዉ ያላቸዉ፡፡ የኦሮሞ ሊሂቃን የጨቃኛ እንዲሁም የተጨቃኛ ታሪክ ነዉ ያላቸዉ፡፡ ስለሆነም የኦነግ የኢትዩጵያ ታሪክ አረዳድ የአንዳንድ የኦነግ ሙሁራን መመረቅያ ፅሑፍ በላይ ሊሆን አይችልም፡፡

አንዳንዶቹ የኢትዩጵያ የመቶ አመት ታሪክ ለማስረዳት ኦነግ እና ህ.ወ.ሓ.ት ለማወዳደር ይሞክራሉ፡፡እንደ ህ.ወ.ሓ.ት አመለካከት የመቶ አመት የኢትዩጵያ ታሪክ የሚጠቅመዉ የአሁና ፊደራላዊት ኢትዩጵያ ቅርፅ የያዘችበት እንጂ የኢትዩጵያ ታሪክ የመቶ አመት ነዉ ማለት አይደለም፡፡ ህ.ወ.ሓ.ት የመቶ አመት ታሪክ ለፊደራላዊ አወቃቀር ለማስረዳት የተጠቀመበት እንጂ እንደ ኦነግ የኢትዩጵያ የመቶ አመት ታሪክ አላት ለማለት አይደለም፡፡ስለሆነም የአቶ ጀዋር መሓመድ ፣ የአቶ መሓመድ ኤደሞ፣ የአቶ ፊዶ ኢባ የኦሮሞ ህዝብ በማስመልከት በአልጀዚራ ያካሄዱት ዉይይት የሙታን መንፈስ ዉይይት በላይ ዋጋ የሚያወጣ አይደለም፡፡ ታሪክም የኦሮሞ ህዝብም አይደግፋቸዉም፡፡

የኢትዮጵያ ተቋዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች የዲሞክራሲ እይታቸዉ ጠባብ ነዉ፡፡

የዲሞክራሲን ሰፊ እይታ ተብሎ ሊከፈል የሚችለዉ ዋናዉ መለክያ ዲሞክራሲ በመካኒካል አካል በላይ ማሰብ የሚችል አመለካከት ሲኖር ነዉ፡፡ ከዚህ በመነሳት አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሳት ይገባናል፡፡ የኢትዮጵያ ተቋዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች የዲሞክራሲዉ እይታዉ መካሊካል ወይስ ሙሉ እይታ (holistic approach) ነዉ ብለን መጠየቅ አለብን፡፡

በዚህ ፀሓፊ እምነት አብቻኞቹ ተቋዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች የዲሞክራሲን እይታቸዉ መካኒካል ነዉ፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነን የፓለቲካ ፓርቲዎቹ የሚያራምዱት የትግል ስልት ነዉ፡፡ የተቋዋሚ ፓለቲከኞች ዋና የትግል መሳርያዉ ሰላማዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ ነዉ፡፡ሰላማዊ ሰልፍ በራሱ ዲሞክራሲ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ በጣም መካኒካል የሚባል የዲሞክራሲ ገፅታ የሚወክል ነዉ፡፡ ሰፊ የዲሞክራሲን እይታ ከሰለማዊ ሰልፍ ብቻ ወጥቶ በሌላ ይዘት ያላቸዉ (substantive matters) በተሻለ ሁኔታዎች አብልጦ ቢያተኩር ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ እድገት የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ሙሉ የዲሞክራሲ እይታ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራሞች የአብዛኛዉ ሕብረተሰብ ፍላጎት ያካተተ ብቻ ሳይሆን ከዲሞክራሲ መንፈስም ጭምር በአንድ ወንዝ እየፈሰሱ መሆናቸዉ ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ በዚህ መሰረት አብዛኞቹ የተቋዋሚ ፓለቲካ ፕሮግራሞች እንዲሁም ይህን ለማስፈፀም የሚያራምዱት የሰላማዊ ሰልፍ መሳርያ የዲምክራሲ ጠባብ መንፈስ ጋር ነዉ የሚዛመደዉ፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ “በአንድነት ስም” የተሰባሰቡ ፓርቲዎች እንደ አንድነት፣ሰማያዊ እና የመሳሰሉት የይዘት ጉድለት ካለባቸዉ ፓርቲዎች አንዱ ናቸዉ፡፡ “የአንድነቶች” የህብረ ብሔር አስተሳሰብ ዲሞክራሲ እና ፓለቲካ አካባቢያዊ ነዉ (democracy and politics is local) የሚለዉ ይዘት ይጎድለዋል፡፡ “የአንድነቶች” ፓርቲ የዲሞክራሲ እና የፓለቲካ መንፈስ የተገነባዉ አገራዊ ነዉ (democracy and politics is national) የሚል ፍልስፍና ነዉ፡፡ ሙሉ የዲሞክራሲ መንፈስ እይታ ደግሞ የትግል ስልት መካኒካል ከመሆኑ በላይ ዲሞክራሲ አካባብያዊ ይዘት እንዳለዉ መረዳት ይጠይቃል፡፡ “የአንድነቶች” ፓርቲ የይዘት ጉድለት ምንጭ ደግሞ “አገራዊ ማቅናት እሳቤ” (nation building thesis) የሚለዉ የተሳሳተ የኢትዮጵያ ታሪክ አነባብ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ “አገራዊ ማቅናት እሳቤ” አራማጆች ሁሌ የዲምክራሲ እይታቸዉ ጠባብ ነዉ፡፡ “የአንድነቶች” ፓለቲካ ፓርቲ እጣ ፈንታ “አገራዊ ማቅናት እሳቤ” ከሚያራምዱ የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም የሕብረ ብሔር ፍልስፍና የሚያራምዱ እንዲሁም የብሔር ብሔረሰቦች መብት የማይቀበል አስተሳሰብ ሁሌ የዲምክራሲዉ እይታዉ አከባቢያዊ ይዘት አለዉ ከሚለዉ የዲሞክራሲ መንፈስ የሚጣረስ ነዉ፡፡ ስለሆነም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ ሕገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም፣ የዲሞክራሲ መንፈስ አካባቢያዊ አይደለም አገራዊ ብቻ ነዉ የሚለዉ እይታ ያለዉ አስተሳሰብ የዲሞክራሲ ሃይል ሊሆን አይችልም፡፡ ኤሌክትሪክ ቴክኒሻን የኤሌክትሪክ ገመዶች አገናኝቶ ብርሃን ሊሰጠን ይችላል ግን የኤሌክትሪክ ንድፈ ሃሳብ ( theory of electricity) ገብቶት አይደለም፡፡ “የአንድነቶች” ሃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ ገብታቸዉ ግን የዲሞክራሲ መንፈስ የገባቸዉ አይመስልም፡፡

የህ.ወ.ሓ.ት የትጥቅ ትግል መዝሙር ፍልስፍ እና የተቃዋሚ ፓለቲከኞችም ፍልስፍና !

የዚህ ፅሑፍ ዋና ጉዳይ የኢትዮጵያ የፓለቲካ ባህሪ ምን መሆን እንዳለበት ለማስረዳት ሲሆን እግረ መንገዴም የህ.ወ.ሓ.ት የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት በነበረ ወቅት አንድ ተወዳጅ መዝሙር ፍልስፍና ለመረዳት ወይም ለማስረዳት ነዉ፡፡ ከመዝሙሩ የመጀመርዎቹ ስንኞች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

ዘይንድይቦ ጎቦ (የማንወጣዉ ተራራ)
ዘይንሸግሮ ሩባ (የማንሻገረዉ ወንዝ)
ፍፁም ወይከ የለን ( ፉፁም ሊኖር አይችልም)
መስመር እዩ ሓይልና (መስመር ነዉ ኃይላችን)
ህዝቢ እዩ ሓይልና (ህዝብ ነዉ ኃይላችን)
ወይከ አይንሳዓርን (ከቶ አንሸነፍም)

ይህችን የመዝሙሩ አካል የኢትዮጵያ ፓለቲካ ምን መሆን እንዳለበት የሚያስረዳ ነዉ፡፡

ቲፕ ኦኔል የተባለ የአሜሪካ ሴኔት አፈ ጉባኤ ስለ ፓለቲካ ድንቅ አባባል ተጠቅሞ ነበር፡፡ ቲፕ ኦኔል ሁሉም ፓለቲካ አካባቢያዊ ናቸዉ(All politics are local) ይላል፡፡ አሁንም በምድረ አሜሪካ የሚሰራበት ያልተፃፈ የፓለቲካ ህግ ነዉ፡፡ አንዳንዴ በምድረ አሜሪካ የከተማ አዳራሽ ዉይይትን/ክርክር (city hall meeting) የሚሉት አይነት ነዉ፡፡ አንዳንዴ የክልል ቴሌቪዥን የሚተላለፉ የህዝብ እሮሮዎች፤ የአሜሪካ የከተማ አዳራሽ ዉይይትን/ክርክር ይመስላሉ፡፡ ስለሆነም ማንኛዉ ፓለቲከኛ እንዲሁም ፓለቲካ ፓርቲ አስተሳሰባቸዉ አካባቢያዊ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አካባቢያዊ ማለት ታች (grass root level) የሚኖረዉ የሕብረተሰብ ክፍል ፍላጎች ጠንቅቆ በመረዳት አብዛኛዉ ህዝብ ሊያስደስት የሚችል የመፍትሄ አማራጭም ጭምር ማምጣትን ያካትታል፡፡ የቀድሞ የኢራን ፕሬዝደንት አሕመዲን ነጃድ ድንቅ ሰዉ ነበሩ፡፡ የኢራን ተራ ህዝብ በጣም የቀረቡ እንዲሁም የህዝባቸዉ ፍላጎት ጠንቅቀዉ የሚረዱ ነበሩ፡፡ ይህ በሌላ አነጋገር ፕሬዝደንት አሕመዲን ነጃድ ፓለቲካ ማለት አካባቢያዊ ማለት ነዉ ብለዉ በቅጡ ተረድተዉ ነበር፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከላይ የተቀመጠዉ መዝሙር የፓለቲካ አካባቢያዊነት ባህሪ የሚያስረዳ ነዉ፡፡ ህዝብ ነዉ ኃይላችን የምትለዉ ስንኛ የፓለቲካ አካባቢያዊነት ባህሪ መገለጫ ነች፡፡ በኢትዩጵያ ፓለቲካ አካባቢያዊ የሚለዉ ሲተረጎም ልዩ መልእክት(pecuniary meaning) ይኖረዋል፡፡ አካባቢያዊነት ማለት የማንነት/ነፃነት ጥያቄ እንዲሁም የሆድ የቀን ፍጆታ መልስ መስጠት ማለት ነዉ፡፡ ታድያ እነዚህ ሁለት ነገራት ጠንቅቆ የሚያቅ ፓለቲካ ፓርቲ የኢትዩጵያ ፓለቲካ ንጉስ ይሆናል፡፡ በህዝብም ዘንድ ተወዳጅ ይሆናል፡፡

አንዳንዴ ፓለቲካ ፓርቲዎች በሚያራምዱት ፍልስፍና ምክንያት መንደርተኛ(ብሔር ተኮር) እንዱሁም አገራዊ (ሕብረ ብሔር ተኮር) ተብለዉ ይፈረጃሉ፡፡ ለምሳሌ ኢህአዴግ “ገበሬ” ነዉ ይባላል፡፡ ኢህአዴግ “ገበሬ” ነዉ ሲባል ፓለቲካ አካባቢያዊ ነዉ የሚለዉ መልእክት ይሰጣል፡፡ ሰማያዊ ወይም አንድነት ወይም ኢዴፓ ፓለቲካ ፓርቲዎች “የከተማ አራዳ” ናቸዉ ሲባል ፓለቲካ አገራዊ ነዉ ማለታቸዉ ነዉ፡፡ “የከተማ አራዳ” የገበሬዉን ችግር ከቶ ለመረዳት አይችልም፡፡ አብዛኛዉ የኢትዩጵያ ህዝብ ደግሞ “የከተማ አራዳ” አይደለም፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርብ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአሜሪካ ኮንግረስ የአፍሪካ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ ቀርበዉ ስለ ኢትዩጵያ ነባራዊ ሁኔታ የሰጡት ምስክርነት “የከተማ አራዳነት” የሚያልፍ አይደለም፡፡ ፓለቲካ ፓርቲዎች አዲስ አበባ እና በጥቂት የክልል ከተሞች ታጥረዉ ብቻ ህዝብ ነዉ “ኃይላችን” ሊሉ አይችሉም፡፡ አገር አቀፋዊ ምርጫ ለማሸነፍ እንዲሁም አዉራ ፓርቲ ለመሆን መጀመርያ የአካባቢያዊ አስተሳበብ መቀበል ይጠይቃል፡፡ በሌላ አባባል በፓለቲካ እይታ “የከተማ አራዳ” ከመሆን “ገበሬ” መሆን ያዋጣል፡፡ስለሆነም አሁንም ህዝብ ነዉ ኃይላችን የሚለዉ ፍልስፍና እንቀበል፡፡

“ አላልካችሁም” ፓለቲካ እና “አዋቂነት” የተቃዋሚዎች ፍልስፍና

የእድገት እና ትራንስፎርመሽን እቅድ ከመጀመርያው ለምንስ የማትችሉት ታቅዳላቹ ለሚሉ አመለካከቶች በተቋዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ቡዙ ጊዜ ይስተዋላል፡፡ ለእንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች መልስ የሚሆን በአንድ መፅሓፋ ያነበብኩት ተገቢ መልስ ይመስለኛል፡፡ ፈረንጆች እንደሚሉት አይሆንም ብሎ ከማሰብ የሚገኝ ጥቅም ቢኖር፣ ችግሩ ሲከሰት “ አላልካችሁም” በማለት የሚገኝ ከንቱ እርካታና መመፃደቅ ብቻ ነዉ፡፡ እንዲህ አይነቱ መመፃደቅና መሬት ጠብ የሚል ጥቅም አይሰጥም፡፡ እንዲህ አይነቱ “ አዋቂነት”፣ ባያገኘዉም በተስፋ ብቻ ለማግኘት እየታገለ የሚሞተዉ “መሀይም” ለአገርም ለራሱም የበለጠ ይጠቅማል ፡፡

ፍፁም ሃላ ቀር ሆነዉ የተነሱና ከአደጉት ላይ ለመድረስ በእጀጉ መሮጥ ያለባቸዉ አገሮች ኢኮኖሚያቸዉ እዚያ ለመድረስ የረዳቸዉ ለእድገት ቅድሚያ የሰጠ መንግስትና አገርን ለማሳደግ ከተነሳ ዉስጣዊ እልህ (የቀድሞ ጠ/ሚኒስተር የአቶ መለስ ቃል ለመጠቀም “ ቁጭት”) ጋር የተደበላለቀ “የኢኮኖሚ ብሄረተኝነት ወይም አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (One Economic Society)” የተላበሰ አካሄድ ነዉ፡፡ የኢትዮጰያ የእድገት እና ትራንስፎርመሽን እቅድ “የኢኮኖሚ ብሄረተኝነት ወይም አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ” ተምሳሌት ነዉ፡፡ The late Prime Minister Meles Zenawi summarized the whole concept in one world while he was asked about the feasibility of the growth and transformation plan by the MPs. He said so what? So, our response will be so what? ምክንያቱም “ አላልካችሁም” የሚል በከንቱ የሚገኝ እርካታና መመፃደቅ ጥቅም ስለ ሌለዉ፡፡

**********

The writer Abiy Chelkeba Worku is ablogger in this blog. He is a lecturer of law at Ambo University and can be reached at [email protected]

Abiy Chelkeba Worku is a blogger in this blog. He is a lecturer at collge of law and governance of Mekelle University and can be reached at [email protected]

more recommended stories