ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር አለፈች

ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር አለፈች፡፡ የሀገር ውስጥ ሚዲያ እንደሚከተለው ዘግቦታል፡፡

*********

ፋና

ለብራዚሉ የ2014 አለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድቡን በ10 ነጥብ እየመራ ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከተከታዩ የደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ተጫውቶ 2 ለ 1 አሸነፈች ።

በጨዋታው ባፋና ባፋናዎቹ ቀድመው ጎል ቢያገቡም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኢትዮጵያ በጌታነህ ከበደ አቻ ሆና ነበር ።

አንድ እኩል የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን ያጠናቀቁት ብሄራዊ ቡድኖቹ በ29ኛው ደቂቃ ላይ ደቡብ አፍሪካውያን በራሳቸው ላይ አስቆጥረዋል ።Ethiopian football team Walia - ahead of the match with South Africa

በመጨረሻም ኢትዮጵያ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር አንድ ጨዋታ እየቀረው ለቀጠይ የመጨረሻ ማጣርያ ውድድር አልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ ከሚያልፉ 10 የአፍሪካ ሀገራት መካከልም አንዱ ሆኗል ፡፡

—-

ኢቲቪ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለመጨረሻ የማጣርያ ውድድር አለፈ፡፡

ለ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ እየተካሄደ ያለው የማጣርያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ዛሬ ሰኔ 9 /2005 ዓ/ም ተጫውቶ 2 ለ 1 አሸነፈ፡፡

ደቡብ አፍሪካ በርናርድ ፓርከር በ 33 ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪነትዋ አስቀድማ ብትይዝም በ43 ደቂቃ ጌታነህ ከበደ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ ያደረገች ጎል አስቆሯል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ተጫዋች ፓርከር በሁለተኛ ግማሽ ጨዋታ በራሱ ባስቀጠራት ግብ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2 ለ 1 አሸንፎ ወጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ አንድ ጨዋታ እየቀረው ለቀጠይ የመጨረሻ የደርሶመልስ ውድድር አልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ ከሚያልፉ 10 የአፍሪካ ሀገራት አንዱ መሆን ችለዋል ፡፡

እንዲሁም ግብፅና ኮትዲባር ከየምድባቸው ለሶስተኛ ዙር የደርሶመልስ ጨዋታ አልፈዋል፡፡

*******

Daniel Berhane

more recommended stories