የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቦትስዋናን አሸነፈ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2014ቱ የብራዚል የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የቦትስዋና አቻው አሸነፈ።

በጨዋታው ጌታነህ ከበደና ሳላህዲን ሰዒድ የአሸናፊነቶቹን ግብ አስቆጥረዋል።

በዚህ ውጤት መሰረትም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምድን ምድቡን በ10 ነጥብ መምራት ችሏል።Ethiopia National Football Team - Walya

ሁለት ጨዋታዎች የሚቀሯቸው ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የዛሬ ሣምንት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉ ሲሆን ቀሪው አንድ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጭ ከሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር የሚደረግ ይሆናል። (Fana – June 8, 2013)

*************

ለ2014ቱ የብራዚሉ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ሰኔ 01/2005 በተካሄደው ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባለሜዳውን የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን 2 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ለኢትዮጵያ ግቦቹን ጌታነህ ከበደና ሳላዲን ሰይድ በመጀመሪያው አጋማሽ በ35ኛው እና በ46ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ ሽመልስ በቀለ የሞከራትንም የግቡ ቋሚ መልሶበታል፡፡ ለቦትስዋና ብቸኛዋን ግብ ቶቦጎ ሴምቦዋ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ 4 ጨዋታዎች 10 ነጥብ በመሰብሰብ ምድቡን በአንደኝነት በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ጨዋታ ቡድኑ በተለይ በአጭር ቅብብል የበላይነቱን ይዟል፡፡ በጨዋታው ሳላህዲን ሰይድ በዳዊት ፈቃዱ፤ ሽመልስ በቀለ በአዳነ ግርማ እና ምንያህል ተሾመ በበኃይሉ አሰፋ ተቀይረዋል፡፡

በማጣሪያው ብሄራዊ ቡድኑ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች የሚቀሩት ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ከደቡብ አፍሪካ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያካሂደው ጨዋታ ወሳኝ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል የነበረው ደጉ ደበበ በጉዳት ምክንያት በዚህ ጨዋታ አልተሰለፈም፡፡ (ERTA – June 8, 2013)

**********

Daniel Berhane

more recommended stories