በባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ

በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በግዜያዊነት ወደሚቆይበት ብሄራዊ ሙዚየም ዛሬ ሚያዚያ 25/2005 ተዛውሯል፡፡

ሃዉልቱ በነበረበት ቦታ የመሬት ዉስጥ የባቡር መስመር ይዘረጋል፡፡Abune Petros statute - Piaza, Addis Ababa Ethiopia

የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር በሃይሉ ስንታየሁ እንዳሉት ሀዉልቱ አስካሁን በነበረበት መሬት ዉስጥ እስከ 20 ሜትር ጥልቀት በመቆፈር ስራዉ ይከናወናል፡፡

የዉስጥ ለዉስጥ ስራው እስከ መጭው ክረምት አጋማሽ ድረስ ተጠናቆ አፈር ይመለስበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ ስራው በተባለው ግዜ ሲጠናቀቅ የአደባባዩንና የመንገዱን ስራ በአዲስ መልክ በመገንባት ሃዉልቱ ወደ ነበረበት ቦታ በቀጣዩ አመት እንዲመለስ ይደረጋል ብሏል፡፡

ሀውልቱ በግዜያዊነት ሲነሳም ሆነ ወደፊት ወደቀድሞ ቦታው ሲመለስ ዉበቱን ከመጨመርና እስካሁን የተጎዱ የሀውልቱን ክፍሎች ከመጠገን ውጭ ምንም አይነት የቅርፅም ሆነ የይዘት ለዉጥ አይደረግበትም::

 ሪፖርተር፤ በዛብህ ታደለ
*************

Source: ERTA – May 2, 2013. Originally titled “የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ”

Daniel Berhane

more recommended stories