በባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ

በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በግዜያዊነት ወደሚቆይበት ብሄራዊ ሙዚየም ዛሬ ሚያዚያ 25/2005 ተዛውሯል፡፡

ሃዉልቱ በነበረበት ቦታ የመሬት ዉስጥ የባቡር መስመር ይዘረጋል፡፡Abune Petros statute - Piaza, Addis Ababa Ethiopia

የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር በሃይሉ ስንታየሁ እንዳሉት ሀዉልቱ አስካሁን በነበረበት መሬት ዉስጥ እስከ 20 ሜትር ጥልቀት በመቆፈር ስራዉ ይከናወናል፡፡

የዉስጥ ለዉስጥ ስራው እስከ መጭው ክረምት አጋማሽ ድረስ ተጠናቆ አፈር ይመለስበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ ስራው በተባለው ግዜ ሲጠናቀቅ የአደባባዩንና የመንገዱን ስራ በአዲስ መልክ በመገንባት ሃዉልቱ ወደ ነበረበት ቦታ በቀጣዩ አመት እንዲመለስ ይደረጋል ብሏል፡፡

ሀውልቱ በግዜያዊነት ሲነሳም ሆነ ወደፊት ወደቀድሞ ቦታው ሲመለስ ዉበቱን ከመጨመርና እስካሁን የተጎዱ የሀውልቱን ክፍሎች ከመጠገን ውጭ ምንም አይነት የቅርፅም ሆነ የይዘት ለዉጥ አይደረግበትም::

 ሪፖርተር፤ በዛብህ ታደለ
*************

Source: ERTA – May 2, 2013. Originally titled “የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ”

5 thoughts on “በባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ”

 1. my brothers,sisters who are the citizens of Ethiopia, let us keep our unique calture that we inherted from the past generation. Our tolerance for human being in general,paying respect for eliders in particular were our brand.However, insalting,blaming,condamening,threatening…become the most known fashion in the current generation,while, the world is a village under globalization.please my dears think positive for the sake of Ethiopia!.All evil intents/acts would harm us. Be the son of the great nation, by shawing the qualties of
  our fathers!.

 2. my brothers,sisters who are the citizens of Ethiopia let us keep our unique calture that we inherted from the past generation. Our tolerance for human being in general,paying respect for eliders in particular were our brand.However, insalting,blaming,condamening,threatening…become the most known fashion in the current generation,while, the world is a village under globalization.please my dears think positive for the sake of Ethiopia!.All evil intent/acts would harm us. Be the son of the great nation, by shawing the qualties our fathers!.

 3. dug,
  በደሃው ህዝብ ሂሳብ እየቆረጥክ የምትበላው፡ጮማ ስብ ሆኖ አይንህን ጆሮህን እና ልብህን ደፍኖታል። ሌብነት አጭበርባሪነት እና አረመኔነት ባልግዜዎችን የሚጠናወት ደዌ ይመስላል።
  ለማንኛውም እስቲ የአቡነዲያብሎስን ሃውልት ለማሻሻል እና ለመጠገን ወደሙዝየም አስገብተን የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት በቦታው “ለግዜው” እናቁመው ፡)
  ደግነቱ ይህ ከምቾት ብዛት የሚመጡት በሽታዎች የዛሬዎቹን ባለስታኖች አንድ በአንድ እያሰናበታቸው ነው። ህዝቡ ይከታተላል። ህዝቡ አይረሳም።

 4. ደጃዝማች ዘውዴ ገብረስላሴ በ ጃንሆይ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ ዘመናዊ ቀለበት መንገድ ሊያሰሩ አቅደው ነበር።ደጃዝማች ዘውዴ ቤታቹ ሊያፈርስ ነው ብለው የዛን ጊዜ ጨለምተኞች ልማቱን አሰናከሉት።እነሱም ምንም ሳይሰሩ ሲፎክሩ እና ሲያቅራሩ፣ጮማ ሲቆርጡ ኖሩ።የ ዛሬዎቹ የባቡር እና የህዳሴው ግድብ ልማት ተቃዋሚዎች የነዛ ጨለምተኞች የልጅ ልጅ ናቸው።ዛሬም ስታይላቸው አልቀየሩም፣ልማቱ ግን አይቆምም ይቀጥላል።

Comments are closed.