Sendek | ከምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ጥያቄ ያነሱ 25 ፓርቲዎች ተመካከ ሩ

• የፓርቲዎች ስብስብ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ነው ተብሎለታል
• የስብስቡ ሰባት ኮሚቴ አባላት በቅርቡ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ

(በዘሪሁን ሙሉጌታ)

በያዝነው ዓመት የሚካሄደው ምርጫ ከመከናወኑ በፊት መፈታት ያለባቸው መሰረታዊ የምርጫ መርኾዎችና የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ መወያየት አለብን ብለው ፒቲሽን ከተፈራረሙት 34 ፓርቲዎች መካከል 25ቱ በጋራ ጥቅሞቻቸው ጉዳይ ተገናኝተው መከሩ።

እሁድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በመድረክ ጽ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከ34ቱ ፓርቲዎች 25ቱ ተገናኝተው በቀጣይ ለቦርዱ በሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የፓርቲዎች ጊዜአዊ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ኤክሲኩዩቲቭ ሆቴል በጠራው ስብሰባ ላይ በዚህ ዓመት በሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ ጊዜአዊ ሰሌዳ ይፋ ከመደረጉ በፊት ምርጫው ነፃ ፍትሃዊና ተአማኒ ለማድረግ ቅድሚያ ውይይት በማድረግ ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረብ ሲሆን በጋራ በሚያግባቡ ጉዳዮችም በቀጣይም ውይይት በማድረግ የጋራ አቋም የመያዝ ዓላማ እንዳለው ከአቶ አስራት ገለፃ መረዳት ተችሏል።

ፓርቲዎቹን እያሰባሰበ ያለው “መድረክ ነው” የሚለው አገላላጽ ከእውነት የራቀ ነው የሚሉት አቶ አስራት ስብስቡ ነፃ ፓርቲዎች በእኩልነት አብረው የጀመሩት እንቅስቃሴ አካል እንጂ አንዱ መሪ ሌላው ተመሪ አለመሆኑንም አያይዘው ተናግረዋል።

ባለፈው እሁድ በተካሄደውም ስብሰባ ላይ ፓርቲዎቹ ባሉት የምርጫ ማካሄድ ችግሮችና በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ መሰረታዊ የፖለቲካ ችግሮች ዙሪያ በማተኮር የጋራ አቋም ለመያዝ የተቻለበት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አስራት አብሮ መስራቱ በየደረጃው እያደገ እንዲሄድ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

ስብስቡ የአጭር ጊዜ እቅድና የረጅም ጊዜ እቅድ በመንደፍ ለቦርዱ ከሚቀርቡ የመወያያ ጥያቄዎች ባለፈ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በማዘጋጀት የሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እንዲያውቀው እንደሚደረግ ከአቶ አስራት ገለፃ መረዳት ተችሏል።

የፓርቲዎችን ስብስብ እንዲያስተባብር ሰባት ሰዎችን ያቀፈ ጊዜአዊ ኮሚቴ መዋቀሩንም ያብራሩት አቶ አስራት ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን አቶ አስራት ጣሴ ከመድረክ፣ አቶ ወንድምአገኘው ደነቀ (ከመላው ኢትዮጵያ አንድት ድርጅት መኢአድ)፣ አቶ ግርማ በቀለ (ከኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት (ኦህዴህ) ፀሐፊ፣ አቶ ስለሺ ፈይሳ (ከሰማያዊ ፓርቲ) ምክትል ፀሐፊ፣ አቶ አለሳ መንገሻ የጌዲዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ጌሕዴድ)፣ አቶ ለገሰ ሳንቃሞ ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና አቶ ኤርጣፎ ኤርዴሎ (የከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ (ከሕብ) ጊዜአዊ አስተባባሪ ሆነው ተመርጠዋል።

በእሁድ እለቱ ስብሰባ ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም ከምርጫው በፊት ለመወያየት 34 ፓርቲዎች ፒቲሽን ቢፈራረሙም 25ቱ ብቻ ሊገኙ የቻሉት አንዳንዶቹ ፓርቲዎች ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው መሆኑን የጠቆሙት አቶ አስራት አንዳንዶቹ የክልል ፓርቲዎች በመሆናቸው መገኘት ባለመቻላቸው ነው። የተቀሩት ደግሞ ከዚሁ ከአዲስ አበባ አባል ለመወከል ቢሞክሩም በህጋዊ ደብዳቤ እንዲወክሉ በመጠየቃቸውና ያንን ባለሟሟላታቸው እንደሆነም አቶ አስራት ተናግረዋል።
በአዲሱ ስብስብ ውስጥ ኢህአዴግ ባለበት የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ውስጥ የሚሳተፉ በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በመገናኛ ብዙኀን ገለፃ
****************
*Originally published on the Amharic weekly, Sendek, on Nov. 7, 2012. Republished here with the permission to do so, without implying endorsements.

Check the drop down menu for posts on related topics.

Daniel Berhane

more recommended stories