Sendek | ታላቁ የህዳሴ ግድብና የግብፅ ስጋቶች [Amharic]

(በፀጋው መላኩ)

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚል ስያሜ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ በአፍሪካ ትልቁን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከጀመረች አንድ ዓመት አልፎ ሁለተኛው ዓመት እየመጣ ነው። አንደኛው ዓመት እንደተጠናቀቀ የግንባታው ሰባት በመቶ መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን፤ ትላንት ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማው በቀረቡት የመንግስት አቋም ግንባታው 11 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል። 97 በመቶው የግብርና ምርቱን በአባይ ውሃ ላይ ጥገኛ ያደረገችው ግብፅ ከግድቡ መገንባት ጋር በተያያዘ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖን ሊፈጥር ይችላል በሚል ሥጋቷን በተለያየ

መንገድ ሥትገልፅ ቆይታለች። ኢትዮጵያ በአንፃሩ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት ከመጉዳት ይልቅ እንዳውም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልፅ ቆይታለች። በኢትዮጵያ በኩል ግድቡ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ባልተጠበቀ ጐርፍ እንዳይጥለቀለቁ፣ ግድቦቻቸው በደለል እንደይሞሉና የወሃ ትነቱንም ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ ሲገለፅ ቆይቷል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በተለይ ግብፅና ሱዳን በግድቡ ግንባታ ላይ ሥጋት ካላቸው አጠቃላይ የግድቡን ሁኔታ የሚመረምር የኤክስፖርቶች ቡድን ተቋቁሞ የራሱን ሞያዊ ሪፖርት እንዲያቀርብ ፈቃደኝነቷን ገልፃለች።

በዚህም መሠረት International Panel of Experts በሚል አንድ ቡድን ተቋቁሞ በህዳሴው የግንባታ ቦታ በመገኘት የራሱን ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። ቡድኑ ስድስት አባላትን ያቀፈ ነው። ቡድኑ ከኢትዮጵያ፣ ከግብፅና ከሱዳን ሁለት ሁለት ኤክስፐርቶችን ያቀፈ ሲሆን ከዚህ ውጪም አራት ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ኤክስፐርቶችን እንዲይዝ የተደረገ ነው። የኤክሰፖርት ቡድኑ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የመጀመሪያውን ጉብኝት በግድቡ አካባቢ በመገኘት ያደረገ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ስብሰባውንም በሰኔ ወር 2004 ላይ አድርጓል። ቡድኑ ከሰሞኑ የመጨረሻ የግድቡን የአንድምታ ተፅዕኖ ጥናቱን አጠናቆ የደረሰበትን ውጤት ለሦስቱም መንግሰታት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

የቡድኑን የመጨረሻ ሪፖርትን ተከትሎ የሚኖሩትን ሂደቶች ጊዜው ሲደርስ የሚታይ ይሆናል። ግብፅም ሆነች ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያላቸውን ሥጋት ለማጥራት ከኢትዮጵያ አንፃር የቡድኑ ጠቀሜታ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ነው የሚነገረው። በመሠረቱ ግድቡ ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት ውጪ ለመስኖ አገልግሎት የሚውልበት ሁኔታ የማይኖር መሆኑ በኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ስለተገለፀ የግድቡ ጉዳይ የአባይን ውሃ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ ለመጠቀም ከሚያስችለው ስምምነት ጋር በቀጥታ የሚያገናኘው ነገር አይኖርም።

ያም ሆኖ ግን የአባይን ውሃ በተመለከተ ግብፅ በ1929 የነበረው የቅኝ ግዛት ውል በነበረበት እንዲቀጥል ፅኑ ፍላጐት ያላት መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልፅ ቆይታለች። በቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ በኩል ተረቅቆ በተግባር ላይ የዋለው ይህ የቅኝ ግዛት ስምምነት (Colonial Treaty) በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረጉ ማናቸውም የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግንባታዎች ከግብፅ ይሁንታ ውጪ እንዳይካሄዱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በላይኞቹ ተፋሰስ ሀገራት እገዳን የሚጥል ነው። ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ1959 ዓ.ም 85 በመቶ የአባይን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጰያን በማግለል ግብፅና ሱዳን 90 በመቶውን የአባይ ውሃ በጋራ ለመጠቀም የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመው ሲተገብሩ ቆይተዋል።

ከዚያ በኋላ በነበሩት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተፋሰሱ ሥር የነበሩት ሀገራት የውስጥ ፖለቲካ የተረጋጋ አለመሆን እነዚህ ሁለት ስምምነቶች አንዳች ጥያቄ ሳይነሳባቸው እንዲቀጥሉ አድርጓቸው ቆይቷል። ጊዜው እየረዘመ በሄደ ቁጥርም ስምምነቶቹ በሌሎች ተፋሰስ ሀገራት ሳይቀር ተቀባይነት ያለው እንዲመስል አድርጐም የቆየበት ሁኔታም ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያም ሆነች ሩዋንዳ፣ ብሩንዲና ሌሎቹ ሀገራት ከጦርነት አዙሪት ወጥተው መረጋጋት ሲጀምሩ የአባይን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በጋራ ለመጠቀም ጥያቄ ማንሳታቸው አልቀረም።

በዚህም መሠረት በተለይ ግብፅና ሱዳንን ባካተተ መልኩ ሌሎቹ የተፋሰሱ ሀገራት በውሃው ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ለመወያየት አንዳንድ እንቅሰቃሴዎች ሲጀመሩ በተለይ ግብፅ በዚህ ዙሪያ ወደ ውይይት ለመግባት ብዙም ፈቃደኝነትን ያሳየችበት ሁኔታ አለነበረም። ሆኖም ከተከታታይ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች በኋላ እ.ኤ.አ በ1999 ዓ.ም ግብፅንና ሱዳንን ጨምሮ የዘጠኝ የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብት ሚኒስትሮች ኦፊሴላዊና መደበኛ በሆነ መልኩ በወንዙ ፍትሃዊ የውሃ ክፍፍል ላይ ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። እነዚህ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ብሩንዱ፣ ሩዋንዳና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኰንጐ ናቸው። ለተወሰኑ ዓመታትም ኤርትራ በታዛቢነት ስትሳተፍ ቆይታለች። በዚህም መሠረት የተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ትብብር ተመስርቶ የቀድሞዎቹን ስምምነቶች በመሻር በአዲስና ዘመናዊ የውሃ ሀብት ክፍፍል ላይ አንድ አይነት መግባባት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድን በመቅረፁ ረገድ ከ10 ዓመት ያላነሰ ጊዜን ፈጅቷል። አብዛኛው ሂደትም ሲጓተት የቆየው በግብፅና በሱዳን እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ሌሎቹን የላይኞቹን ተፋሰስ ሀገራት በማስተባበሩ ረገድ ሰፊ የዲፕሎማሲ ስራን በመስራቱ በመጨረሻ እ.ኤ.አ በ2010 የአባይን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል በአምስት የተፋሰሱ ሀ

Daniel Berhane

more recommended stories