ውዳሴ ባንዳነት በቴምብር – የ”ኢትዮጵያ” ደራሲዎች ማህበርና የፖስታ ቤት ምፀት

(በተስፋኪሮስ አረፈ )

የ‹‹ኢትዮጵያ›› ደራሲዎች ማህበር ከኢትዮጵያ ፖሰታ አገልግሎት ጋር በመተባበር የማስታወሻ ቴምብር ከተዘጋጀላቸው የአማርኛ ደራሲዎች ዝርዝር ዉስጥ የአፈ ቀይሳር አፈወርቅ ገ/የስ ስም ሳይ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያውያን ግራዚያኒ በአገሩ ሊሰራለት የታሰበውን ሃወልት እንድንቃወም በትጋት እያስታወሱን ባለበት ወቅት የራሳችን ገራዚያኒ አዚሁ ሃወልት እያሰራንለት ነው? እና ለምን የአማርኛ ቋንቋ ደራሲዎች ብቻ ተመረጡ? የሚል ጥያቄዎች ይዤ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ <<ኢትዮጵያ>> ደራሲዎች ማህበር ጎራ አልኩ፤

1. ጥያቄ አንድ – አፈወርቅ ገ/የስ ኢትዮጵያ በጣሊያን እንድትገዛ(ቅኝ ገዛት ስር እንድትሆን) ሽንጣቸውን ገትረው የሞገቱ ሰው ሆነው እያለ (በጣሊያን መወረራችንን ይደግፉታል) እንዴት የማስታወሻ ቴምብር ይሰራላቸዋል? ልብ አድርጉ፤ የሮማ ካቶሊክ የጣልያንን ጦር ባርካ በመሸኘቷ ነው ይቅርታ እንድትጠይቅ ኢትዮጵያውያን እየተሟገቱ ያሉት፡በሁሉቱ መካከል ልዩነት ይኖር ይሆን? ማህበሩስ ባዘጋጀው ብሮሸር የአፈ ቀይሳርነት ማእረግ ከጣሊያን መንግስት እንዴት ማግኘት እንደቻሉ ለምን አልገለፀውም?

ከማህበሩ ያገኘሁት ምላሽ፡- እኛ ለአማርኛ ስነፅሁፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ እንጂ የሰዎቹ ግለ ታሪክ አናይም፡፡

የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው ማለት መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ ግን ለተማሪዎች ስናስተምር የአፈወርቅን ባንዳነት ወይስ ለአማርኛ ስነፅሁፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ ወደ አእምሮአቸው ቀድሞ እንዲመጣ የምንፈልገው?

2. አፈወርቅ ከባንዳነታቸው በተጨማሪ የሚታወቁት በዘር ጥላቻ ፅሁፋቸው ነው፡፡

ዳግማዊ አጤ ምንሊክ በሚል ለአፄ ምንሊክ እጅ መንሻነት በፃፉት መፅሃፋቸው (አስቡት እነደገና በታተመው የመፅሃፉ ሽፋን ላይ የመቶ አመት ባለፀጋ ታላቅ መፅሃፍ ይላል)

ምንሊክ በነገሰልነና ይህ አምበጣ ትግሬ በጠፋልነ እያለ የማመኝ ሰው በኢትዮጵ አልነበረም” ( ገፅ 48)

ጎጃምን የመሰለ ደግ አገርም ሶስት ወር ሙሉ በትግሬ አንበጣ ተመደመደ” (ገፅ 52)

የትግሬ ወታደር በዚያ ጉረሮ በሚፍቅ ቋንቋው ኩሪ ኩሪ እያለ እርጉዝ አስወረዳት፤ እመጫት ጡቷ ደረቀባት” (ገፅ 54)

ብለው ፅፈው ነበርና ለሽልማት ካበቃቸው አንዱ መስፈርት ይኼ ይሆን ብሎ መጠርጠር ይቻል ይሆን?

3. ጥያቄ ሁሉት፡- ደብተራ ፍስሃን እንዴት አላካተታችሁትም?

በማህበሩ ፅ/ቤት ያገኘኋቸው ሰው ምላሽ፡ ደብተራ ፍስሃን አንድ አፄ ምንሊክ ላይ ችግር ያለበት ፍትህ ጋዜጣ ላይ የሚፅፍ ዮናስ የሚባል ልጅ ሲጠቅሰው ስሙን አስታውሳለሁ፡፡

የኔ ማብራሪያ –

‹‹ደብተራ ፍስሃ ማለት የነ አፈወርቅ ዘመን ሰው(Contemporary) ነው፡፡ ጦብላህታ የሚል ርእስ ያለው የትግርኛ ልብ ወለድ ፅፏል፡፡ ደብተራ ፍስሃ የመጀመሪያ የትግርኛ ልብ ወለድ የደረሱት እ.አ.አ. 1895 ሲሆኑ አፈወርቅ ግን የመጀመሪያ የአማርኛ ልብ ወለድ የደረሱት(የታተመው) በኛ አቆጣጠር 1900 ነው፡፡የመጀመሪያ የአማርኛ ልብ ወለድ ደራሲ መሆን ያሸልማል፡፤ የመጀመርያ የትግርኛ(የኢትዮጵያ?) ልብ ወለድ ደራሲ መሆን ግን እንኳንስ ሊያሸልም ስምህ እንኳን አይታወቅም፡፡ እና የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማህበር ሳይሆን የአማርኛ ቋንቋ ደራሲዎች ማህበር መባል ነው ያለባችሁ ››

የሚል ድምዳሜየን ከተናገርኩ በኋላ ተጨማሪ ጥያቄ ሰነዘርኩ-፤ ‹‹ ምን ያህል በእንግሊዘኛ ቋንቋ የፃፉ ኢትዮጵያውያን ደራሲዎች አሏቹህ? ››

የማሕበሩ ሀላፊዎች አንድ ሶስት የሚሆኑ ደራሲዎችን ከጠቀሱልኝ በኋላ ‹‹The shadow of my company›› የሚል ርእስ ያለው ልብወለድ ደራሲስ ታውቁታላቹህ የሚል ጥያቄ ስወረውር መልሱ አናውቀውም ሆነ፡፡

አንደኛውን በማህበሩ ላይ ያለኝ አስተያየት ተዛብቷልና ‹‹ ደራሲውን ያላወቁት ደራሲው ትግራዋይ (የትግራይ ሰው) ያውም የህወሓት ታጋይ የነበረ ስለሆነ ይሆን? ›› የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮየ መጣ፡፡

4. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲትዩት በቢፒአር ጥናት ታጥፎ ‹‹ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ›› ሲሆን፤ የዲፓርትመንቱ (የትምህርት ክፍል) ሃላፊው በምክን

Daniel Berhane

more recommended stories