በፌስቡክ ሜዳ (በሰርካለም ቦጋለ) [Amharic]

ድንገት በጐዳና ላይ ሲሄዱ ከአሁን ቀደም በውል የማያውቁት ሰው አጥብቆ ሰላም ቢልዎትና ሊያወጋዎም ቢከጅል የት ታውቀኛለህ? ብሎ መደንፋትና ተገላምጦ መሄድ የለም። ምክንያቱም በማህበረሰቡ ድረገጽ ጐዳናFacebook እንተዋወቅ ብለው እራስዎን ይፋ አድርገው ቀርበዋልና ነው፡፡

የፌስቡክ ጓደኝነት ጅማሮው በአንድ የጽሑፍ መልእክት መነሻነት አልያም በድረ ገፁ ማህደር ባሉ ፎቶዎች መስህብነት ሊሆን ይችላል፡፡ «ወዳጅነቴን ተቀበለኝ» ብሎ ጥያቄ ያቀረበው ጠያቂ የይሁንታ መልስ እየተሰጠው አንድ ብሎ ከሺዎች አልፎ እስከ ሚሊዮን የሚደርሱ ጓደኞችን ያፈራል።

ይህ የማህበረሰብ ድረገጽ 150,000,000 በላይ ተጠቃሚዎችን በዓለም ዙሪያ የሚያስተናግድ እንደመሆኑ መጠን የሚፈለጉትን ሰውና ተሞክሮ ወይም መልእክቶቹን ለመጋራት እንዲሁም መረጃዎችንና አጠቃላይ እውቀቶችን ለመካፈል የሚያስችል ነው፡፡ በዚህ ድረ ገጽ በፎቶና በቪዲዮ የታገዘ ምስልና ድምጾ ችንም ማከል ስለሚያስችል ይረባል ያሉትን ፍሬ ነገር ከራስ አልፎ ለወዳጅ ለማቀበል እንዲሁም ለመቀበል ጥሩ የግንኙነት ድልድይ ነው፡፡

ሆኖም «አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል» እንዲሉ አንደበታችን በሆነው የፌስቡክ ድረ ገፅ ላይ የምንቀርፃቸው መልእክቶች አመለካከት፣ አላማና ዝንባሌያችን ቁልጭ አድርጐ ያሳያሉ።

ሃሳብን መሰንዘር፣ ያወቁትንም ለሌሎች ማካፈል ነውር ባይሆንም በፌስ ቡክ ሜዳው ላይ ‘የኔን ሃሣብ ተጋሩ’ በሚል የግል አመለካከታቸውን በብዙኃኑ ላይ ለመጫን የሚጥሩ ነውረኛ ግለሰ ቦች በብዛት ይስተዋላሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በአብዛኛው ስማቸውንና ፎቶአቸውን በግልጽ የማያኖሩና ከመጠሪያ ስማቸው ባሻገር ያሻቸውን ስም ሰይመው በከፈቱት ድረ ገጽ ‘በሬ ወለደ’ የሚል የሃሰት መልዕክቶችን በተለያየ አቅጣጫ ሲያሰራጩ፣ ብዥታን ሲፈጥሩና ፀብ ጫሪ መልዕክቶችን ሲያደርሱ ይስተዋላሉ፡፡ ከዚህም አልፎ ባህልን፣ ሃይማኖትንና ሥርዓትን በጣሰ መልኩ ግብረገብነት የጐደላቸውን ምስሎች የቴክኖሎጂውን አማራጭ ተጠቅመው የአንዱን ምስል ከሌላው እየገጣጠሙ ሰብአዊ ክብርን በጣሰ መልኩ የሚያቀርቡና የተቀናበረ መረጃ ፈጥረው ቀውስን መፍጠር የሚፈልጉ ሰዎች አሉ።

ታዲያ የሚገርመው እነዚህ ግለሰቦች የራሳቸው ባልሆነ ስምና ፎቶ አልባ በሆነው አልያም ማንነታቸውን በማይገልጸው አድራሻቸው ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ በተዘረጋው የፌስቡክ መረብ ፀያፍ መልእቶችን ማድረሳቸው ብቻ አይደለም። አመለካከታቸው በፍፁም ከእነሱ በማይገጥምና ድርጊታቸውን ከሚፀየፉ ግለሰቦች ጋር ጭምር ተመሳስለው በሚፈጥሩት ጓደኝነት መስመር በመጠቀም እነዚህን አስነዋሪ ፎቶ የቪዲዮና የጽሑፍ መልእክቶች ታግ ወይም ሼር እያደረጉ የባለቤቶቹ ልሳን ያልሆነውን መልእክት አስመስሎ የማሠራጨቱ ነገር ብዙዎችን ሲያወዛግብ መታየቱ ነው።

የድረገፁን አጠቃቀም ሥርዓት ጠንቅቆ ባለማወቅና በቸልታ ክፍት በሚደረጉ የግንኙነት መስመሮችን በመጠቀም የግል አስተሳሰብን የብዙኃኑ አድርጐ የማስተላለፍ፣የሌሎችን ፈቃድ ሳያገኝ በሌላው ላይ መልእክቱን ማስፋት በራሱ ነውረኛ የሚያሰኝና የግለሰብን መብት የሚጥስ አግባብነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ በመነሻዬ እንዳልኩት ፌስ ቡክ ነፃ የማህበረሰብ ድረገጽ እንደመሆኑ እውነተኛውም ሐሰተኛውም ገንቢና አፍራሽ መልእክቶች ሊተላለፍበት ይችላል። መልእክቶቹን መከልከልና መገደብ ባይቻልም በማወቅና ባለ ማወቅ ድረ ገፃቸውን በአግባቡ ሳይዘጉ ለሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ድረገፁን ሌሎች እንዲጠቀሙ የሚያስችለውን ፈቃድ ያለገደብ የሚሰጡ ለአደጋው ተጋላጭ ናቸው። ድረገጹን ያለ አግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች የግል ሃሳባቸውን እያጋሩ የሰዎችን ትክክለኛ ማንነትና አስተሳሰብ በተዛባ መልኩ በማስተላለፍ ከመስመራቸው ፈቅ ብለው እንዲታዩና በሌሎች አመኔታ እንዲያጡ ያደርጓቸዋል። ይህም በማህበራዊ፣በፖለቲካዊና በግል ሕይወት ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል አይሆንም አንድ ወይም ጥቂት ግለሰቦች የሰሩትን በብዙኃኑ ላይ ታግ በማድረግ በቅጽበት የሚያስተላልፉት መልእክት የሚፈጥረውን መጥፎ ገጽታ በዓመታት እንኳን ማጥራት ሊቸግር ይችላል፡፡

የዚህ ጥፋት ሰለባዎችን ጥቂት ገጠመኞች ላውራችሁና የዛሬውን በዚሁ ልቋጭ። ሰውየው ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ናቸው፡፡ በስራ ቦታቸውና በሚኖሩበት አካባቢ የተከበሩት እኚህ ሰው በከፈቱት የፌስ ቡክ ድረ ገጻቸው ላይ የራሳቸውና የቤተሰቡ ሁሉ ፎቶ ስለሰፈረ በእሳቸው ብቻ ሳይሆን በባለቤታቸውና በልጆ ቻቸው አማካይነት ፎቶውን ያየ የድረ ገፁ ተጠቃሚ ሁሉ እንዲያውቃቸው አስችሏል፡፡ ታዲያ እኒህ ሰው በቤታቸውና በቢሮ አካባቢ ባላቸው ኮምፒዩተር የመጠቀም እድል ተጠቅመው ገፁን ይክፈቱት እንጂ አዘውትረው የሚገለገሉበት አልነበረም። ታዲያ አንድ እለት በድረ ገፃቸው የታየው ፎቶ ያየውን ሁሉ ያሳቀቀና ያሸማቀቀ ነበር፡፡ በፌስቡክ ድረ ገፃቸው የተለቀቀው ፀያፍ የዝሙት ፎቶ ቤታቸው ደርሶ ኑሮ ለመስክ ስራ ወጣ ካሉበት ወደ ጐጆአቸው ሲመለሱ ጐጆአቸው አዝሞ ነበር የጠበቃቸው። ስለሚባለው ነገር ምንም እንደማያውቁ የገለጹትን መቀበል የቻለ ማንም አልነበረም፡፡ ቀላል የቴክኖሎጂ ቅንብር የታከለበት ይህ መልእክት ቀላል የማይባል ዋጋ ተከፍሎበት የሰውዬው ትዳር ከብዙ ፈታኝ መከራ በኋላ ከመበተን መትረፉን ሰምቻለሁ፡፡

ድረ ገፁን በአግባቡ ለ

Daniel Berhane

more recommended stories