Recent

ወያነ-ትግራይና የሉዓላዊነት አጀንዳ | Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty

[Trouble reading: Download the article in PDF|169 kb ]

መንደርደሪያ

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሰሞኑን ‹‹በኤርትራና በትግራይ ይኖሩ የነበሩ የኤርትራና የትግራይ ዜጐች ተግተው ኢጣልያንን ቢወጉ ኖሮ ከሐረር፣ ከሀድያና፣ ከሲዳሞ፣ ከሸዋ… ወደmesfin_woldemariam ሰሜን መዝመት አያስፈልጋቸውም ነበር፤ ይህ ቢሆን ዛሬ ሌሎች ያልሞቱትን ሞት በመሞታቸው አይወቀሱም ነበር›› የሚል አስገራሚ አስተያየት አስደምጠውናል፡፡ የምላስ ወለምታ ነው እንዳይባል በጽሁፍ ነው፡፡ መብራራት የሚያስፈልጋቸው ሀረጎች ቢኖሩም፤ ሰውየው ‹ኢትዮጲያዊነት›/‹ግለሰባዊነት› ወዘተ የሚሉ ጭንብሎቻቸውን በይፋ ማውለቃቸው ይመስላል፡፡ እርግጥ ጭንብሉ ድሮውንም ማንም አላደናገረም፡፡

ያም ሆነ ይህ የሰውየው ንግግር ለአፍታ ወደ ታሪክ ማህደር መመለስን ግድ ብሏል፡፡ በመሆኑም ለመንደርደሪያ ይህን በየካቲት 2000 ዓ.ም. ተጽፎ ነገር ግን ‹‹አዲሰ ነገር›› ጋዜጣ ሊያትመው ያልፈቀደው እናም ሳይታተም የቆየ ጽሁፍ ላካፍላችሁ፡፡

ጋዜጣው ለማተም ያልፈቀደበት ምክንያት ምንም ሚስጥር የለውም፡፡ ጋዜጣው ይህን ጽሁፍ ጥሎ ሲያበቃ ከጥቂት ወራት በኋላ ያተመው የፕ/ር መሳይ ከበደን ‘the underside of the Eritrean Issue’ የተሰኘ ጽሁፍ ነበር፡፡ ትኩረት የሚስበው የመሳይ ከበደ ጽሁፍ በጭብጥ የዚህ ጽሁፍ ተጻራሪ እና የመረጃ ፋይዳው አናሳ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአዲስ ነገር አዘጋጆች የመሳይ ከበደን ጽሁፍ ከ12 ወራት በፊት ከታተመበት ከኢትዮ-ሚዲያ ዌብሳይት ወስደው ወደ አማርኛ ተርጉመው ማተማቸው ነው፡፡ በነገራችን ላይ የመሳይ ከበደ ጽሁፍ ጭብጥ ‹‹ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጲያ አንድነት በጥብቅ የሚደግፍ መሆኑን እና የትግራይ ኤሊቶች ደግሞ ኤርትራውያን ፖለቲካና ኢኮኖሚ እንዳይቀናቀኗቸው ሲሉ የኤርትራን መገንጠል እንደሚፈልጉት ›› ማሳመን ነው፡፡ የዚህ ወቅታዊ አንድምታ የጽንፈኛ ተቃዋሚዎችን ከኤርትራ መንግስት ጋር መሞዳሞድ ምክንያታዊ ለማድረግ ሲሆን በታሪካዊ ገጽታው ደግሞ የትግርኛ ተናጋሪዎች መለያየት የራሳቸው/በተለይም የትግራይ/ ጥፋት ነው የሚል ሀሳብ ነው፡፡

አሁን ፕሮፌሰሩ መስፍን በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡

እንዲያውም ‹‹ በኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸፋፍኖ የቆየውን እናፍረጥርጠው ከተባለ ለማን አሳፋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው›› ሲሉም ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ ድሮውንም ያለፈ ታሪክ ለምን ይወራል ሲሉ የነበሩት እሳቸውና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡ ሀሳባቸውን ከቀየሩም መልካም፡፡ የቀኝ አክራሪው ክፍል ፊታውራሪ ናቸውና – እንደሳቸው ሚሊዮኖችን በጅምላ መኮነን ሳያስፈልግ – ጥሬ ሀቆችንና የታሪክ ሰነዶችን በተከታታይ በዚህ ብሎግ ላይ በማቅረብ መልስ መስጠት ግድ ይላል፡፡

አሁን ወደጽሁፉ፡፡

[Trouble reading: Download the article in PDF|169 kb ]

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (2)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (3)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (4)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (5)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (6)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (7)

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty [8]

Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty (9)

Source: HornAffairs.com

ይህን ጽሑፍ ወስደው ሊያትሙ ቢሹ እባክዎ የፀሐፊውን ስም እና ምንጩን (ከLink ጋር) ይጥቀሱ፡፡

Fetsum Berhane
About Fetsum Berhane (15 Articles)
Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

10 Comments on ወያነ-ትግራይና የሉዓላዊነት አጀንዳ | Woyane-Tigray and the Question of Sovereignty

 1. fucken idots always talk about tigray….b/c they were ruled and killed from their ancvesstory

 2. እኔ እምለው ዛሬ ላይ በርግጥ የብሄር ለዩነት የለም? በአንድ የሰራ ሃላፊነት ላይ ለመቀመጥ የትግራይ ብሄር ሆኖ መገኘት እንደ መመዘኛ አይታይም?

 3. Dani, it was nice to see excerpts from Terarochin Yanketekete Tiwlid and other TPLF sponsored studies after so long. Although a pro Weyane discussion, equating Tigray peoples’ struggle with Weyani is not fair. Your references were all from TPLF and you reached at a conclusion very much flawed. Tigray’s youth have fought even against TPLF as much as they fought against Derg- you should know that!!

  I would advise you to go to Mekele- Semaitat Hawult Museum and scan for a book or newsletter that clearly talks about TPLF’s understanding of Colonialst Ethiopia over Eritrea. Let us not deny facts.

  And I do not think the Arena folks would go in to spoiling their history for cheap political gains. Do not fool yourself there are a lot of live witnesses on the issue all around Tigray- Mekele; ask TPLF members themselves who know the situation.

  Next time I would hope to see you refer to non partisan resources or do not take sides to attack their current opponents like Aregash.

  thanks,

 4. I am afraid we are talking about two unrelated things. I have never met Prof. Mesfin or Duce Mussolini and proably you know things I don’t. Thanks for the exchange. I now can say I know you just a little better.

  • My friend,
   we are talking about perfectly the same thing.

   Mefin W/Mariam exhibited racism and chauvenism in his comment. He insulted the generation of Alula Abanega as having a shameful history.

   You don’t see a problem in his comment.

   But, I do.

   In fact, this is probably the worst comment this guy ever made in his life.

   Than for sharing yours views.(consider joining the hot discussion on my facebook wall). Keep in touch.

   • I can see you are angry – whether legit or not. Assuming your pic is current you look much younger than Prof. Mesfin and yet you call him “this silly man” in addition to “racist like Mussolini and Hitler” and “chauvenist”. You are not serious, are you? Don’t you think the comparison is too severe and unfair? I believe you know your history enough to not be engaging in such labels. Good talking with you. Have a good weekend.

 5. Dear Daniel,
  Either you don’t understand Amharic or you have an axe to grind. I rechecked the professor’s article and what I found was no nearer to what you posted. The professor was merely illustrating Sebhat’s mode of argument and not making a statement you allege he was making. The option for you is to apologize and make corrections accordingly. I hope you would publish this comment. Alem.

  “ይህ አባባል እምብዛም ትርጉም የለውም፡፡ ወተት ቢኖር በእንጀራ አምገህ ትበላ ነበር እንዳለችው ሴትዮ ነው.. ቢሆን ኖሮ በማለት ክርክሩን ለመለወጥ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በኤርትራና በትግራይ ይኖሩ የነበሩ የኤርትራና የትግራይ ዜጐች ተግተው ኢጣልያንን ቢወጉ ኖሮ ከሐረር፣ ከሀድያና፣ ከሲዳሞ፣ ከሸዋ… ወደ ሰሜን መዝመት አያስፈልጋቸውም ነበር፤ ይህ ቢሆን ዛሬ ሌሎች ያልሞቱትን ሞት በመሞታቸው አይወቀሱም ነበር፤ ከኋላዬ ሁለት ተጨማሪ ዓይኖች ቢኖሩኝ፣ ቁመቴ አስር ሜትር ቢሆን፣ …እያሉ መከራከር የትም አያደርስም፡፡ ለልብ-ወለድ ስራ እንጂ ለታሪክ አይበጅም፤ የተዛባ አስተሳሰብ የሆነውንና ያልሆነውን፣ ያለፈውንና የሚመጣውን፣ እውነትና ሐሰትን ለይቶ በግልጽ እንዳያዩ አእምሮን ይጋርዳል፡፡ ስለዚህም አእምሮ ክፍት፤ ህሊና የፀዳ ሲሆን ለመግባባት ያመቻል፡፡

  ስብሓት …..ታሪካችን ይጠና፣ ይመርመር፣ ይጻፍ፣ ህዝቦች

3 Trackbacks & Pingbacks

 1. ‘Addis-Neger’: when deceit becomes the norm « Danielberhane's Blog
 2. ምላሽ ለፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም – በፕ/ር ገብሩ ታረቀና በአማኑኤል መሓሪ « Danielberhane's Blog
 3. Tigray| ምላሽ ለፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም – በፕ/ር ገብሩ ታረቀና በአማኑኤል መሓሪ « Danielberhane's Blog

Leave a comment

Your email address will not be published.


*