Dergue officials pardon | ከሃይማኖት መሪዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ [full text]

በደርግ ዘመን የተፈጸሙ በደሎችንና ጥፋቶችን በአገራዊ ይቅርታና ዕርቀ ሰላም ለመጨረስ ከኢትዮጵያ የአራቱ ቤተ እምነቶች የሃይማኖት መሪዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ

የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣
እኛ የኢትዮጵያ የአራቱ ቤተ እምነት የሃይማኖት መሪዎች ፣
– የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
– የኢትዮጵያ እስልምና ጉዲዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤
– የኢትዮጵያ ካቶሉካዊት ቤተ ክርስቲያን፤
– የኢትዮጵያ ወንጌሊዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤
በደርግ የአገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን በደልና ጥፋት በይቅርታና በዕርቅ ለመጨረስ እንዲቻል ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ቆይተናል፡፡ ለዚሁም መነሻ የሆነን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በፍርድ ሥር የሚገኙ የደርግ ባለሥልጣናትና በተለያየ የሥራ ደረጃ ላይ ይሠሩ የነበሩ ታራሚዎች በዘመኑ በፈጸሙት በደልና ጥፋት ተጸጽተው ፈጣሪ አምሊክ፣ ይቅርታንና ምሕረትን እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ እኛም በቦታው በተገኘንበት ወቅት ይቅርታ እንድናደርግላቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትም እንደዚሁ ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው የኑዛዜና የይቅርታ ደብዳቤያቸውን በመስጠት የይቅርታና ዕርቅ መድረክ እንድናዘጋጅላቸው ጠይቀውናል፡፡ በዚህም መሠረት በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና በመመካከር የእያንዳንዱን ቤት ያንኳኳውን ይህን የታሪክ ጠባሳ በአገራዊ ይቅርታና ዕርቅ መጨረስ ከሁሉ በላይ ታላቅ መንፈሳዊ አንድምታ ያለው በመሆኑ እነሆ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንኑ መንፈሳዊ ጥሪ ተቀብል በጎ ምሊሽ እንደሚሰጠን በመተማመን ይህን የሰላምና የዕርቅ ሀሳብን ይዘን ቀርበናል፡፡

የተከበራችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣

አገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ከውጭም ሆነ ከውስጥ የተነሱ ብዙ ችግሮችን አሳልፋለች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በተለያየ የታሪክ ምዕራፍ መጠነ ሰፊ ግጭቶችን በመከላከልና ዳር ድንበሩን በማስከበር አንድነቱን ጠብቆ የመኖር ባህሉን አዳብሯል፡፡ ይህም ሂደት በኢትዮጵያውያን ዘንድ የአገር ወዲድነትንና በጋራ አብሮ የመኖርን መንፈስ ፈጥሮ ያለፉ መሆኑን ታሪክ የሚመሰክረው ሀቅ ነው፡፡
በአገራችን የነበረው የደርግ አስተዳደር የዜጎች ተቻችሎ፣ ተማምኖና ተስማምቶ የመኖርን መንፈስ ያዛባ ስለነበር በሰዎች መካከል የርስ በርስ ጥፋትንና በደልን አስከትሏል፡፡ ወቅቱም በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የኀዘን ካባ ጥሎ ያለፈ ክስተት እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በነበረው ኢሰብአዊ ድርጊት የሞቱ፣ የተበተኑ፣ የተሰደዱ፣ ያለጧሪ፣ ቀባሪ የቀሩ፣ የስቃይ ሰለባ የነበሩ ወገኖች መኖራቸው የማይካድ እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም ፈጣሪ ትዕግሥቱንና ጽናቱን ለመላ ሕዝባችን ሰጥቶ በዚህ አሰቃቂ ሒደት ውስጥ አልፈን አገራችን ዛሬ በልማት ወደፊት ተራምዳ፤ በሕዝቦቿ ጥረት ሁለንተናዊ ዕድገት እየታየና የተስፋ ጉዞ ምዕራፍም ተጀምሮ ለማየት በመብቃታችን ፈጣሪያችንን እናመሰግናለን፡፡
ይህም ሁሉ ሆኖ በዘመኑ ጥፋት የፈጸሙ ወገኖችና የስቃዩ ሰለባ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሰላምና በመቻቻል አብረው እየኖሩ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህ አብሮ፣ ተቻችልና ተማምኖ በአንድነት የመኖር ባህሌ ከፈጣሪ ያገኘነው ሌዩ ጸጋ ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ በረከትና የጋራ ዕሴትም ለዚህ ትውልድ ትምህርት እንዲሆንና እንዱጎለብት የማድረግ ኃሊፊነት አለብን፡፡ ሕዝባችንም ይህን የዕርቅ ጥሪ ተቀብሎ የሰላምና የፍቅር ኑሮ እንዲኖር መላ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፈጣሪ ስም አደራ እንላለን ፡፡

የተወደዳችሁ ወገኖቻችን ፤

እኛ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ባለብን ሃይማኖታዊ ኃሊፊነት በደል አድራሹንና በደለል የደረሰበትን ወገን በሙሉ ያለፈውን መጥፎ ታሪክ ለፈጣሪያችሁ አቅርባችሁ የደም ዕዳ መዝገብ ተዘግቶ ልጆቻችን ቂም በቀልን መውረስ አስወግደው በሰላም፣ በፍቅርና በመቻቻል እንዲኖሩ ወደፊትም ተመሳሳይ አስከፊ ድርጊት በኢትዮጵያ ታሪክ ፈጽሞ እንዳይደገም የዕርቅንና የይቅርታ መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት በመተማመን ደፍረን አቅርበናል፡፡
እኛ የሃይማኖት መሪዎች በደለል አድራሹ ወገን የጥፋቱን ክብደት ተረድቶ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ በደል የደረሰበት ወገንም ስለ ፈጣሪ ብሎ ያለፈውን መራራ የሕይወት ጉዞ ወደኋላ በመተው የይቅርታና የርኅራኄ መድረክ ማዘጋጀት እንዳለበት እናምናለን፡፡ለይቅርታና ለዕርቅም ቅድመ ሁኔታ የሊቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይቅርታን እንዲያደርግ ስንማፀንም የጥፋቱን ክብደት በመዘንጋት አይይሆም፤ ሁላችንም የዚህ አስከፊ ዘመን የስቃይ ሰለባዎች ነበርን ፡፡ በታሪኩ ውስጥም ያለፍን ስለነበርን ይህን የታሪክ አሉታዊ ገጽታ በራሳችን የሕይወት ተሞክሮ እናውቀዋለን፡፡ ይሁንና የይቅርታን ሙሉ ትርጉም የምናገኘው ሁላችንም መንፈሳዊ በረከቱን ስንካፈል ነው፡፡

የተወደዳችሁ የአገራችን ሕዝቦች ፤

በልባዊ ይቅርታ የተገነባ ሕዝብ ዘላቂ ሰላምና ልማት ይኖረዋል፡፡ የሰላምና የመቻቻል መንፈስም በኅብረተሰቡ ውስጥ ልማትን ያጎለብታል፤ ዘላቂነቱም አስተማማኝ ይሆናል፡፡ ዛሬ የአገራችን ዜጎች ለልማት ሥራ በተነሣሱበት ወቅት ቂም በቀልን አስወግዶ ኅብረተሰቡን ከከፋ ድኅነት ለማውጣት የሚደረገው ጥረት መንግሥትና ሕዝብ የተያያዙትን አቅጣጫ ያጠናክራሌ፡፡ በይቅርታና በምሕረት የተነሳም ልብ ሁሉን ያሸንፋል፡፡ በመከባበር፣ በመቻቻሌና በመተማመን አብሮ የሚኖረውን ሕዝብ ፈጣሪ አምላክ ይባርከዋል፡፡ የሕዝቡም የኑሮ ደረጃ ያድጋል፣ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ወደ በረከት ይለወጣሌ፣ ድኅነትና ኋላ ቀርነትም ይሸነፋሉ፡፡

ይህ በአገራችን ላይ የደረሰውም ክስተት በየዘመኑ በሌሎች አገሮችም በተመሳሳይ ሁኔታ ለብዙ ሰዎች ኅልፈት፣ መበታተንና መሰደድ ምክንያት እንደሆነ ይታወቃሌ፡፡ ነገር ግን ጊዜው ሲያልፍ መንግሥታት ሲለዋወጡ ሕዝቡ ያለፈው አስከፊ ገጽታ ለትውሌድ እንዳይተላለፍ በይቅርታና በዕርቅ አስወግደው ከቂምና በቀል ተላቀው ለአገራቸው ገጽታ መለወጥ በዓለም ምሳሌያዊና አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸሙ ሕዝቦችን ልምድ መውሰድ ተገቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ በአህጉራችን በደቡብ አፍሪካ፣ በሩዋንዲና በሌሎችም ተመሳሳይ አገሮች የተፈጸመው የታሪክ ጉዞ በቂ መረጃችን ነው ፡፡ ስለሆነም ይህ ትውሌድ የቂምና የበቀሌ ውርስን አስወግዶ፣ የሰላም የዕርቅና፣ የመተማመን፣ የመቻቻልና ተቀራርቦ አብሮ የመኖር የተቀየሰውንም ባህሌ ልናወርሰው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ሰው ሆኖ የማይበድልና ፈጣሪን ይቅርታ መጠየቅ የማይገባው ፍጡር የለም፡፡ ፈጣሪ አምሊክም ይቅርታን ለሚጠይቁ ሁለ ይቅር ባይና ምሕረትን ሰጪ ነው፡፡
የደርግ ባለሥልጣናትና በተለያየ የአስተዳደር እርከን ላይ የነበሩ በቃሉቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎችም በፈጸሙት ጥፋትና በደሌ ተጸጽተው ፈጣሪ አምላክን፣ ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ እኛም ከበደሉ አድራሾች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን ይቅርታና ዕርቅን፣ የሰላምታ መለዋወጥን አድርገናል፤ በመቀጠልም በደሌ አድራሾቹ የኢትዮጵያን ሕዝብና መንግሥት ይቅርታ ለመጠየቅ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት በመግለፅ የይቅርታ ጥያቄያቸውን አቅርበውልናለል፡፡ አንድ መድረክ ተፈጥሮላቸው ሕዝቡንና መንግሥትንም ይቅርታ እንዲጠይቁ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ተማፅነዋል፡፡
ስለሆነም ይህ የዕርቅ ሀሳብ በደርግ ዘመን የተፈጸመውን በደለልና ጥፋት በአገራዊ ይቅርታና ዕርቅ ለመጨረስ በየትኛውም ጎራ ተሠልፎ ሲፋለም የነበረ ሁሉ ሕይወቱንና ኑሮውን ከቂም በቀል አጽድቶ የዚህ አገራዊ ይቅርታና ዕርቅ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያችንን በፈጣሪ ስም እናቀርባለን፡፡

በዘመኑ የተፈጸመው በደሌ ፈጣሪንም ሰውንም ያሳዘነ በመሆኑ በጋራ ምሕረትንና ይቅርታን ልንጠይቅ ይገባል፡፡ ሁሉም የአገራችን ዜጎች በደሌ አድራሾችና በደል የደረሰባቸው ቤተሰቦች፣ የተወሰነባቸውን ፍርድ ጨርሰው የወጡ እንኳ ቢኖሩ ከዚህ መንፈሳዊ የዕርቅ በረከት ተካፋይ እንዱሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡
* ይህንም ከፍተኛ አገራዊ ጉዳይ ለማስፈጸም የሃይማኖት መሪዎች ከየቤተ እምነቱ የተውጣጣ ዓቢይ ኮሚቴ አቋቁመው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሠሩ ቆይተዋል፤ በመሥራትም ላይ ይገኛሉ፡፡
* በሃይማኖት መሪዎች የተጀመረው የሰላምና የዕርቅ ሥራ ከአገራችን ተሐድሶ አንድ አካሌ በመሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አካላት ጉዳዩን እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡
* በደርግ የአገዛዝ ዘመን በተፈጸመው በደልና ጥፋት ሰለባ የሆኑ ማኅበራትን በማወያየትና በመመካከር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በተለይም ከስቃይ ሰለባ ማኅበር መሪዎች ጋር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት አከናውነናለል፡፡ በቀጣይነትም የማኅበሩ መሪዎችና አባላት ከዓቢይ ኮሚቴው ጋር በመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠሩ ነው ፡፡ እንደዚሁም ከሰማዕታት ሀውልት ግንባታ ማኅበር መሪዎችም ጋር አብረን ስንሠራ ቆይተናል፡፡
* በደርግ የአገዛዝ ዘመን የተፈጸመው በደልና ጥፋት መጠነ ሰፊና መላ የአገሪቱን ክልል ያዳረሰ እንደመሆኑ በደሌ አድራሾቹንና የስቃይ ሰለባ የሆኑትን ሁሉ ይሁንታን ለማግኘት የይቅርታና ዕርቅ ጥሪ መልእክትን ይዘው የየቤተ እምነቱ ተወካዮች የሚገኙበት ብዛት ያላቸው የሰላም ልኡካንን ልከናል፡፡ ሁለንም የአገሪቱን ከተማዎች ለማዳረስ ተሞክሯል፡፡ በዚህም አገራዊ ጉዲይ ላይ ውይይትና ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛል፤ ሥራውም በመልካም ሁኔታ እየተካሔደ ሲሆን፣ ከእነዚህም ከተሞች ሁለት ሁለት ተወካዮች ተመርጠው በጠቅሊሊው ከ500 በላይ የሚሆኑ የስቃይ ሰለባ ፣ የተጎጂ ቤተሰቦች፣ የአገር ሽማግል ተወካዮች የሚገኙበት አዱስ አበባ ከተማ ላይ ታኅሣሥ 16 ቀን 2003 ዓ.ም የይሁንታ (ይቅርታን የመቀበል) ስብሰባ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡ በዚሁ ዕሇት ከበደሌ አድራሹና በደል ከደረሰበት ወገን የሚገኘውን ይቅርታና ዕርቅ በመቀበል ጉዲዩ ሇመንግሥት እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
* መንግሥት በእኛ በሃይማኖት መሪዎች የቀረበውን የይቅርታና የዕርቅ ሀሳብ እንደተቀበለን በታኅሣሥ ወር መጨረሻ 2003 ዓ.ም የደርግ ዘመን በደልና ጥፋት በብሔራዊ ደረጃ በይቅርታና በዕርቅ ተዘግቶ የሰላምና የዕርቅ በደል በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ይበሰራል፡፡
* በኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች የጋራ ሥራ ለአፍሪካና ለዓለም ምሳሌ የሆነ ታላቅ የሰላምና የዕርቀ ሰላም ማዕከል የመመሥረት እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡
* በዚህ በዓል ላይ በደሌ አድራሹና በደሌ የደረሰበት ፊት ለፊት ተገናኝተው ይቅርታና ዕርቀ ሰላሙን በመቀባበል ብሔራዊ ሰላምን ያበስራል፡፡ ወጣቶችና ሕፃናትም የዕርቀ ሰላም ዝማሬን ያቀርባሉ፡፡ ከአባቶች ለትወልድ የሚተላለፍ የሰላምና የዕርቀ ሰላም ችቦንም ይቀባበላሉ፡፡ የመቻቻል፣የመተማመንና አብሮ የመኖር መንፈሳዊ ባህልንም ያዳብራል፡፡
*በደርግ ዘመን በተፈጸመው በደልና ጥፋት በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ አካሌ ጉዳተኞች የአእምሮ ሕመምተኞች ሆነዋል፣ ያለጧሪ፣ ቀባሪ የቀሩ ፣ የተበተኑ፣ የተሰደዱ እንዳሉም ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዚህንም ወገኖች ሊያስባቸው ይገባል፡፡ በተለይም ተጎድተው ይቅርታ ያደረጉትን ፈጣሪ አምላክ በምሕረቱና በቸርነቱ እንደሚጎበኛቸው እናምናለን፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እነዚህን ወገኖች በተቻለው አቅም እንዲያግዛቸው ለማድረግ ከቤተ እምነቶች የሚወከሌ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎችም የበላይ ጠባቂ በመሆን ሥራውን ይከታተላሉ፤ በዚሁ አጋጣሚ በዚሁ ቅዱስ ተግባር በሚወጣው መርሀ ግብር መሠረት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡

ይህን አገራዊ ጉዳይም ለመፈጸም ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እሙን ነው፡፡ በዚህም ሥራ ላይ መሳተፍ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነትና ተግባር በመሆኑ ቤተ እምነቶች በጊዜው የሚያስፈልገውን ወጪ አድርገናል፡፡ ይህም ጉዳይ የእኛው እንደመሆኑ፣ እኛው ኢትዮጽያውያን ችግሩን በጋራ ብንፈታው ይሻላል የሚል እምነት ሲሆን፡፡ በዚህም መሠረት የተወሰኑ ታዋቂ ግለሰቦችንና አገር በቀል ድርጅቶችን በመጋበዝ በዚህ ሥራ ላይ ከኛ ጋር እንዱሠሩ በጠየቅናቸው መሠረት ሂሳቡን በሙሉ ልብ በመደገፍ ተሳትፎ አድርገዋል ፡፡
ይህን በተመለከተ እስካሁን ድረስ የተባበሩን ሁሉ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ቀሪውንም በመፈጸም የሁላችንንም ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ በሰላሙ አምላክ ፈጣሪያችን ስም አደራ እንለላለን ፡፡

የሒሳብ ቁጥራችን ‹‹የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሪዎች የጋራ ሥራ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥላሴ ቅርንጫፍ ቁጥር 90631›› ነው፡፡

ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ !
አሜን !
የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤
የኢትዮጵያ እስሌምና ጉዲዮች ጠቅሊይ ምክር ቤት፤
የኢትዮጵያ ካቶሉካዊት ቤተ ክርስቲያን፤
የኢትዮጵያ ወንጌሊዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤
ታህሣሥ 9 ቀን 2003 ዓ.ም.

Daniel Berhane

more recommended stories